አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 16/2017(ኢዜአ)፦ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ ባዳዳ(ዶ/ር) ከፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሉዊስ አንቶኒ ጋር በኢትዮጵያ ያለውን የጀማሪ ስራ ፈጠራ(ስታርታፕ) ሥነ-ምህዳር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።
የፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ ከአውሮፓ ህብረት እና ኤክስፐርቲስ ፍራንስ ጋር በመተባበር የስታርታፕ ሥነ-ምህዳሩን ለማጠናከር10 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ለማድረግ እንደተዘጋጀም ተገልጿል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ ባዳዳ(ዶ/ር) ከፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሉዊስ አንቶኒ ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የጀማሪ ስራ ፈጠራ (ስታርታፕ) ሥነ-ምህዳር ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።
የፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ ከአውሮፓ ህብረት እና ኤክስፐርቲስ ፍራንስ ጋር በመተባበር የስታርታፕ ሥነ-ምህዳሩን ለማጠናከር10 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ለማድረግ እየተዘጋጀ መሆኑ በውይይቱ ወቅት ተገልጿል።
ይህም ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረውንና በቅርቡ ወደ ስራ የሚገባውን የስታርታፕ አዋጅ ወደ ተግባር ለማሸጋገር እንደሚረዳ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።
በተጨማሪም የስታርታፕኢንኩቤሽን ሞዴሎችን ማሻሻል እና የስታርታፖች አቅም ማጠንከርና የፈንድ ምንጮችን ለመጨመር መግባባት ላይ ተደርሷል።
ሚኒስትር ዴኤታው እና ዳይሬክተሩ በኢትዮጵያ ያሉ ስታርታፖች በአውሮፓና ፈረንሳይ የስታርታፕ ስነምህዳር እንቅስቃሴዎች ላይ ተሳትፎ የሚያደርጉብት ዕድል በሚፈጠርበት ሁኔታ ላይ በጋራ እንደሚሰሩም ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025