
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 16/2017(ኢዜአ)፦ የጊቤ 3 የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ5ሺህ 430 ጊጋ ዋት ሰዓት በላይ ኃይል ማመንጨቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።
የጊቤ 3 የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከዕቅዱ በላይ ኃይል ማምረቱን የጣቢያው የኦፕሬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ደጀኔ ጉታ ገልጸዋል፡፡

ከማመንጫ ጣቢያው በ2017 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት 4ሺህ 725 ነጥብ 56 ጊጋ ዋት ሰዓት ኢነርጂ ለማመንጨት ታቅዶ 5ሺህ 436 ነጥብ 5 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ማምረት መቻሉንም ተናግረዋል፡፡
ይህም ከዕቅዱ የ710 ነጥብ 94 ጊጋ ዋት ሰዓት ወይም የ15 ነጥብ 04 በመቶ እንዲሁም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ189 ነጥብ 65 ጊጋ ዋት ሰዓት ወይም የ3 ነጥብ 61 በመቶ ብልጫ እንዳለውም አስታውቀዋል፡፡

አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ማምረት የሚያስችሉ የፍተሻና የክትትል ሥራዎች በየጊዜው መከናወናቸው፣ የኦፕሬሽን ሥራው የተቋሙ ሥራ አመራር ባፀደቀው የኦፕሬሽን ሥራዎች የአሰራር ስርዓት ማኑዋል መሰረት መከናወኑ እና የኃይል መቋረጥ አመላካቾችና ችግሮች(alarms and faults) ሲስተዋሉ ወዲያውኑ እንዲወገዱ መደረጋቸው ለውጤቱ ምክንያቶች ናቸው ብለዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ መጨረሻ 6ሺህ 141 ነጥብ 49 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን አስታውሰው ባለፉት ዘጠኝ ወራትም ከአጠቃላይ ዕቅዱ የ88 ነጥብ 52 በመቶ አፈጻፀም ማስመዝገብ ተችሏል ነው ያሉት፡፡
ይህም በበጀት ዓመቱ ለማመንጨት የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት አመላካች እንደሆነም አቶ ደጀኔ ጉታ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026