አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 18/2017 (ኢዜአ)፦የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ወገኖች ላይ ጫና እንዳያሳድር የታቀዱ የድጋፍ መርሐ ግብሮች መከናወናቸውን የብልጽግና ፓርቲ አስታወቀ።
በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራው የገቢ አሰባሰብ መሻሻሉ፣የልማት ፋይናንስ ዕድገት መመዝገቡ፣የወጪ አስተዳደርና የዕዳ ጫና ማቃለል ላይ ውጤታማ ለውጦች መመዝገባቸውም ተገልጿል።
የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለሁለት ቀናት ያካሔደው ጉባኤ ተጠናቋል።
የጉባኤውን መጠናቀቅ ተከትሎ በወጣው መግለጫ፤ የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ማኅበራዊና ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች በዝርዝር ተዳሰዋል፡፡
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች ላይ ጫና እንዳይፈጠር፣ለደመወዝ፣ ለዘይት፣ለሴፍቲኔት፣ለመድሃኒት፣ ለነዳጅ እና ለማዳበሪያ ከፍተኛ የድጎማ በጀት መመደቡ ተመላክቷል።
በዚህም ለማዳበሪያ 62 ቢሊዮን ብር፣ ለሴፍቲኔት 41 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር፣ ለነዳጅ 60 ቢልዮን ብር፣ ለመድኃኒት 3 ነጥብ 5 ቢልዮን ብር፣ ለምግብ ዘይት 6 ነጥብ 1 ቢልዮን ብር፣ እንዲሁም ለደመወዝ 38 ነጥብ 4 ቢልዮን ብር ድጎማ መደረጉን በመግለጫው በዝርዝር ቀርቧል።
ባለፉት 9 ወራት ብቻ 344 ሺህ 790 የውጭ ሀገር ሕጋዊ የሥራ ዕድሎች እና ከ3 ሚሊዮን በላይ የሀገር ውስጥ የሥራ ዕድሎች መፈጠራቸውም ነው የተገለጸው፡፡
የልማት ተቋማትን በአዲስ አስተሳሰብና በአዲስ መንገድ መልሶ ለማደራጀትና ለመምራት መቻሉን ያመለከተው መግለጫው፥ እያስገኘ ያለው ውጤትም ለሌሎች አርአያ መሆኑን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው መገምገሙ በመግለጫው ተጠቅሷል።
የውጭ ምንዛሬ ክምችት እንዲሁም የባንኮች ተቀማጭ ገንዘብ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ 9 ወራት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ዕድገት ማሳየቱም በመግለጫው ተመልክቷል፡፡
የተሟላ ማክሮ የኢኮኖሚ ማሻሻያ የውጭ የልማት ፋይናንስ ግኝትና ፍሰትን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደጉን ፤ የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ማሻሻያ መደረጉም ትልቅ ለውጥ ማምጣቱን መግለጫው ጠቅሷል።
ማሻሻያው አካታች የኢኮኖሚ ግንባታንና የኑሮ ጫናን ማቅለልን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እየተተገበረ መሆኑም ተብራርቷል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025