
የሌማት ትሩፋት ኢንሼቲቭ አርሶ አደሩን ሀብት እንዲያፈራ እና ተጠቃሚ እንዲሆን ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠረ ይገኛል።
በዳውሮ ዞን ሎማ ወረዳ ኤላ ባቾ ቀበሌ የሚገኙ አርሶ አደር ደነቀ ሳንሞ በንብ ማነብ ሥራ ላይ ተሰማርተዋል።
አርሶ አደሩ ከ600 በላይ በሚሆኑ የዘመናዊ እና ባህላዊ የንብ ቀፎዎች ላይ ነው የንብ ማነብ ሥራ በመስራት ላይ የሚገኙት።
በ10 የተለያዩ መንደሮች ንብ በማነብ ላይ የሚገኙት እኚህ አርሶ አደር በአማካይ በዓመት እስከ 400 ኪሎ ግራም የተጣራ እንዲሁም 200 ኪሎ ግራም የማር ምርት እንደሚያገኙ ተናግረዋል።
ከዚሁ የማር ምርት በየዓመቱ ወደ 400 መቶ ሺህ ብር የሚጠጋ ገቢ እያገኙ እንደሆነ ገልጸዋል።
ለሥራቸው ስኬታማነት ከባለሙያዎች የሚያገኙት ድጋፍ አቅም እንደሆናቸው ጠቅሰው በሚያገኙት ገቢ ሀብት መፍጠር መቻላቸውን አስታውቀዋል።

የሞዴል አርሶ አደሩን ተሞክሮ የተከተሉ በወረዳው የሀሊአኒ አይሺ እና ኤላ ባቾ ቀበሌ አርሶ አደሮችም በንብ ማነብ ሥራ ተጠቃሚ እየሆኑ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
የሎማ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘለቀ ሲሳይ በወረዳው የሌማት ትሩፋት ሥራ በርካቶችን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል ይላሉ።
ተግባሩን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የክትትልና ድጋፍ ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመልክተዋል።
የሎማ ወረዳ ግብርና፣ አካባቢ ጥበቃና ህብረት ሥራ ልማት ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ እና የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መስፍን ገበየሁ የአርሶ አደሩን ተሞክሮ ለማስፋት የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።
በወረዳው ለሚገኙ 14 የማር መንደሮች 220 ዘመናዊ ቀፎ ፣ የማር ማጣሪያ እና የንብ መነቢያ ቁሳቁሶች መከፋፈላቸውንም ጠቁመዋል።
የወረዳው ግብርና ፣ አካባቢ ጥበቃና ህብረት ሥራ ልማት ጽህፈት ቤት የንብና ሐር ልማት ባለሙያ ሙሉነሽ ከበደ አርሶ አደሩ የማር ምርታቸውንም እስከ አዲስ አበባ በመላክ እየሸጡ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።
ምርቱ ጥራቱን የጠበቀ እንዲሆን ክትትል እየተደረገ መሆኑን ስለመግለጻቸውም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመለክታል።
አዲስ አበባ፤ሰኔ 2 /2018 (ኢዜአ)፦የዕቃ ማከማቻ ደረሰኝ ሥርዓት ደንብ የግብርና ኢኮኖሚ ሽግግርን በማሳለጥና የገጠር ልማትን በማጎልበት አርሶ አደሮችን ተጠ...
Jun 10, 2026
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 1/2018 (ኢዜአ)፦ በመዲናዋ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን በማላቅ የተገልጋዮችን እርካታ የሚያሳድጉ ሰው ተኮር ተግባራት ተጠናክረው እንደ...
Jun 9, 2026
ሀዋሳ ፤ ግንቦት 28/2018 (ኢዜአ) ፦በይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ማቀነባበሪያ ፓርክ ከአምራች ኢንዲስትሪዎች ጋር በተፈጠረላቸው የገበያ ትስስር ...
Jun 6, 2026
ነገሌ ቦረና፤ ግንቦት 19/2018(ኢዜአ)፦ የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት መጀመር የአካባቢውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የበለጠ የሚያ...
May 28, 2026