
ጅማ፣ሚያዚያ 27/2017(ኢዜአ)፦የንብ ማነብ ስራን በዘመናዊ መንገድ በማከናወን የማር ምርትን ለማሳደግ የተጀመረው ስራ ይጠናከራል ሲሉ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ገለጹ።
በጅማ ከተማ የማር ኤግዚቢሽን የተከፈተ ሲሆን በኤግዚቢሽኑ ላይ የፌዴራል፣የክልልና የዞን የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም ማር አምራቾችና ነጋዴዎች ተሳትፈዋል።
ሚኒስትሩ በወቅቱ እንደገለጹት፥ ኢትዮጵያ ለንብ ማነብ ስራ ምቹ ሁኔታ ያላት ሀገር ናት።
ከዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም ለማሳደግ ባህላዊውን የንብ ማነብ ስራ ወደ ዘመናዊ መቀየሩ በትኩረት እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።
በተለይም በኦሮሚያ ክልል ለማር አምራቾች ዘመናዊ ቀፎ በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ተደራሽ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
የማር ምርትን ለማዘመን ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ እንደ ሀገር 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዘመናዊ ቀፎ መሰራጨቱን የገለጹት ሚኒስትሩ ከዚህም 250 ሺህ ቶን የማር ምርት ተገኝቷል ብለዋል።
የንብ ማነብ ስራን የበለጠ በማዘመን ከዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም ለማሳደግ የተጀመሩ ስራዎች እንደሚጠናከሩ አስታውቀዋል።
የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ጉቱ ገመቹ በበኩላቸው፥ በክልሉ ከአራት አመት በፊት የተጀመረው የማር ምርት ኢኒሼቲቭ ትልቅ ውጤት እያስገኘ መሆኑን ገልጸዋል።
እየተካሄደ በሚገኘው የማር ምርት ኢኒሼቲቭ ባህላዊ የንብ ቀፎን በዘመናዊ በመተካት የማር ምርት በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል።
በክልሉ የማር ምርትን ለማሳደግ በተደረገ እንቅስቃሴ በዚህ አመት 140 ሺህ ቶን ማር መገኘቱን ተናግረዋል።
የጅማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ቲጃኒ ናስር፣ በዞኑ በግብርና ልማት ኢኒሼቲቮች የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል::
በዞኑ በሁሉም ወረዳዎች እየተተገበሩ ያሉ ኢኒቬቲቮች ውጤታማ መሆናቸውን ገልጸው፥ በማር ምርትም የተሻለ እመርታ መታየቱን ጠቅሰዋል።
በማር ምርት ኢግዚቢሽኑ የተሳተፉ አምራቾች በበኩላቸው፥ መንግስት በተመጣጣኝ ዋጋ ባቀረበላቸው የዘመናዊ ቀፎ ምርታቸው መጨመሩን ገልጸዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026