አዲስ አበባ፤ ግንቦት 2/2017(ኢዜአ)፦ በፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ በላይሁን ይርጋ የተመራ የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን በአፍሪካ የሰዎችና ህዝቦች መብቶች ቻርተር ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ ነው።
በጋምቢያ ባንጁል የአፍሪካ የሰዎችና ህዝቦች መብቶች ኮሚሽን ዋና መሥሪያ ቤት እየተካሔደ ባለው ስብሰባ ላይ በአፍሪካ የሰዎችና ህዝቦች መብቶች ቻርተር (ባንጁል ቻርተር) ወቅታዊ የኢትዮጵያ አፈጻፀምና በአፍሪካ የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (ማፑቶ ፕሮቶኮል) መነሻ ወቅታዊ አፈጻፀም ላይ ልኡኩ ሪፖርቶችን ማቅረብ ጀምሯል።
ሚኒስትር ዴኤታው ለኢዜአ እንደገለጹት ኢትዮጵያ በሪፖርት ዘመኑ በቻርተሩና ፕሮቶኮሉ መሰረት ያሉባትን ግዴታዎች ለመወጣትና የሰብአዊ መብቶችን ከማስጠበቅ አንጻር የተወሰዱ የፖሊሲ፣ የህግ እና ተቋማዊ እርምጃዎችን የሚመለከቱ ለውጦች ሪፖርት በዝርዝር ቀርቧል።
በኮሚሽኑ መርሃ-ግብር መሰረትም ሪፖርቱን ተከትሎ ከኮሚሽነሮች ለተነሱ ጥያቄዎች ኢትዮጵያ በልዑካን ቡድኑ አማካኝነት ሰኞ ግንቦት 4 ቀን 2017 ምላሾችን ትሰጣለች ተብሎ እንደሚጠበቅም ሚኒስትር ዴኤታው ጠቁመዋል።
መድረኩ ኢትዮጵያ በባንጁል ቻርተር እና በማፑቶ ፕሮቶኮል ስምምነቶች መሰረት በአገሪቱ የሰብዓዊ መብቶችን እና የፆታ እኩልነትን ለማጎልበት ያላትን ቁርጠኝነት የምታሳይበት እንደሆነም ተገልጿል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025