አዳማ፤ ግንቦት 1/2017(ኢዜአ)፦ የአከባቢ ብክለትን ለመከላከልና ተፅዕኖውን ለመቋቋም ለሚደረገው ጥረት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እገዛ ተጠናክሮ እንደሚቀጠል ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ።
5ኛው ዓለም አቀፍ የጥናትና ምርምር ሲምፖዝየም በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።
በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈፃሚ ኤባ ሚጀና(ዶ/ር)፤ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የምርምር ስራዎች የማህበረሰቡን ችግሮች የሚፈቱ ሊሆኑ እንደሚገባ ገልጸዋል።
በመሆኑም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቋቋም ለሚደረገው ጥረት እገዛቸው ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አረጋግጠዋል።
የምርምር ሲምፖዚየሙ ዓላማም የፕላስቲክና የወረቀት ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ እንዲሁም የግብርና እና የኢንዱስትሪ ተረፈ ምርቶችን አያያዝ፤ መልሰው መጠቀምና ወደ ሃብት መቀየርን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን አንስተዋል።
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዘዳንት ተሾመ አብዶ(ዶ/ር)፤ ዩኒቨርሲቲው በሳይንስና ቴክኖሎጂ ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ሃይል ከማፍራት ባለፈ ችግር ፈቺ የምርምር ስራዎች ላይ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
በተለይ በህዋ ሳይንስ፤ ፋርማሲዩቲካል፤ ድሮን ቴክኖሎጂና አውቶሞቲቭን ጨምሮ አምስት የልህቀት ማዕከላትን ወደ ሙሉ የምርምር ስራ ለማስገባት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ዩኒቨርሲቲው 20 ክልላዊና የፌዴራል ሜጋ ፕሮጄክቶችን የማማከር ስራ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው በአይሲቲ መሰረተ ልማት ዝርጋታና በሶፍትዌሮች ልማት ላይ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በምርምር ሲምፖዝየሙ ከሀገር ውስጥ ዩኒቨርሲቲዎች፤ ከደቡብ ኮሪያ፤ ከህንድና ከአውስትራሊያ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና የምርምር ተቋማት ተሳታፊ ሆነዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025