የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በክልሉ ለሚካሄደው የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ሁሉም የዕድሉ ተጠቃሚ ሊሆን ይገባል- ርእሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

May 12, 2025

IDOPRESS

ወላይታ ሶዶ፤ግንቦት 1/2017 (ኢዜአ)፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለሚካሄደው የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ሁሉም የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ጥሪ አቀረቡ።


በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ እና ሌሎችም የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተወካዮች በተገኙበት ተጀምሯል።


በዚሁ መርሃ ግብር እስከ ሰኔ 2017 ዓ.ም በክልሉ 900 ሺህ ዜጎችን የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ባለቤት ለማድረግ እቅድ መያዙም ታውቋል።


በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፤ የኢትዮጵያን የዲጂታል ኢኮኖሚ ጉዞ ለማረጋገጥ በመንግስት ከፍተኛ ጥረትና ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።


ለዚህም የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮጀክት አንዱ መሆኑን ጠቅሰው፥ ዲጂታሉን ዓለም በመቀላቀል ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለማግኘት ሁሉም የፋይዳ ምዝገባ ማድረግ እንዳለበት አስገንዝበዋል።


በክልሉ ለሚካሄደው የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ሁሉም የዕድሉ ተጠቃሚ ሊሆን ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።


በክልሉ ከዛሬ ጀምሮ ለሚከናወነው የፋይዳ ምዝገባ አስከ ሰኔ 2017 ዓ.ም 900 ሺህ ዜጎችን የዲጂታል መታወቂያ ባለቤት የማድረግ እቅድ መኖሩን ጠቅሰው፥ እድሉን ተጠቀሙበት በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።


የክልሉ መንግስት ለስራው መሳካት አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል የሚያደርግ መሆኑንም አረጋግጠዋል።


በክልሉ ከዛሬ ጀምሮ እየተካሄደ ባለው ምዝገባም በርካቶች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለመሆን እየተመዘገቡ መሆኑም ገልፀዋል።


በክልሉ በዘመቻ የተጀመረው የምዝገባ ስርዓት እስከ ክልሉ ገጠር አካባቢዎች ድረስም ተደራሽ እንደሚሆን ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ ነው</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...

Feb 28, 2025

<p>በዞኑ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ ነው</p>

ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...

Feb 24, 2025

<p>የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተደረገ ነው - ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል</p>

አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...

Feb 24, 2025

<p>ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች ነው -የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...

Feb 12, 2025