አዲስ አበባ፤ግንቦት 4/2017 (ኢዜአ)፡-የአፍሪካ ህብረት የዘላቂ እዳ አስተዳደርን አስመልክቶ ያዘጋጀው ኮንፈረንስ ዛሬ በቶጎ ሎሜ መካሄድ ጀምሯል።
ኮንፈረንሱ እየተካሄደ የሚገኘው “የአፍሪካ የመንግስት የእዳ አስተዳደር አጀንዳ፤ዘላቂ የእዳ አስተዳደርን የሚያረጋግጡ ስትራቴጂዎችን መተግበር” በሚል መሪ ሀሳብ ነው።
በመክፈቻው ስነ ስርዓት ላይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ብሉ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ ከባቢ አየር ኮሚሽን ሞሰስ ቪላካቲ፣ የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀሐፊ ክላቨር ጋቴቴ፣ የጋና ፕሬዝዳንት ጆን ድራማኒ ማህማ የአፍሪካ ሀገራት የፋይናንስ ሚኒስትሮች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የአፍሪካ ፋይናንስ ተቋማት፣ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
በአፍሪካ ወቅታዊ የእዳ ሁኔታ ላይ በመምከርም የሀገራት የዘላቂ እዳ አስተዳደር ተሞክሮ መለዋወጥ እና አፍሪካ በእዳ የጋራ አቋም ለመያዝ የሚያስችላት ምክረ ሀሳቦች ማቅረብ የኮንፈረንሱ ዋንኛ አላማ መሆኑን ኢዜአ ከህብረቱ ያገኘው ያመለክታል።
በአህጉሪቷ ላለው የእዳ ቀውስ ምላሽ ለመስጠት አሁናዊ የዓለም የፋይናንስ መዋቅር መደረግ የሚገባቸውን ሪፎርሞች በተመለከተም ውይይት ይካሄዳል።
ዘላቂ የእዳ አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን አማራጭ የፋይናንስ ምንጮችን ማስፋት በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ምክክር ይደረጋል።
በአፍሪካ ዘላቂ የእዳ አስተዳደርን ለመፍጠር የሚያስችሉ ውጤታማ የእዳ አስተዳደር አማራጮችን በተመለከተ የመፍትሄ አማራጮች እንደሚቀርቡ ተገልጿል።
ውይይቱን ተከትሎ የአፍሪካ ሀገራት የእዳ አስተዳደር፣የዓለም የፋይናንስ ስርዓት ማሻሻያ እና ዘላቂ የፋይናንስ አስተዳደርን አስመልክቶ የጋራ አቋም መግለጫ እንደሚያወጡ ይጠበቃል።
የአፍሪካ ህብረት የዘላቂ እዳ አስተዳደር ኮንፍረንስ እስከ ግንቦት 6 ቀን 2017 ዓ.ም ይቆያል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025