አዲስ አበባ፤ግንቦት 4/2017(ኢዜአ)፡-በአዲሲቷ የተስፋ አድማስ ኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ጊዜው አሁን ነው ሲሉ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ገለጹ።
በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ 2025 የቢዝነስ ፎረም የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ፣ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮችና የበርካታ ሀገራት ኢንቨስተሮች በተገኙበት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ኢትዮጵያ በዓለም ፈጣን ኢኮኖሚ እያስመዘገቡ ካሉ ሀገራት አንዷ ነች።
ሀገሪቱ የአምራች ኃይልና የበርካታ ወጣቶች መገኛ መሆኗን ጠቅሰው፥ በርካታ የልማት አቅሞችን በመጠቀም ወደ ውጤት እየቀየረች የምትገኝ አዲሲቷ የተስፋ አድማስ መሆኗንም ተናግረዋል።
ሰፊ የገበያ ዕድልን ጨምሮ ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ በመኖሩ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ጊዜው አሁን ነው ብለዋል።
ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ማሻሻያ መደረጉም ከፍተኛ ሀገራዊ ዕድገት ከማስመዝገብ ባለፈ ለውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ስበት መጨመር በር ከፍቷል ነው ያሉት።
የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ፥ ኢትዮጵያ ሰፊ መሬት፣ ከፍተኛ የውሃ ሀብት፣ወጣትና የተማረ የሰው ኃይል እንዲሁም የተሟላ መሰረተ ልማት ያላት ሀገር መሆኗ ለኢንቨስትመንት ምቹ አድርጓታል ብለዋል።
ኢትዮጵያ የተገበረችው የኢኮኖሚ ማሻሻያ፣ተቋማዊ እና መዋቅራዊ ችግሮችን የሚፈቱ ሪፎርሞች ዘላቂ ሀገራዊ ዕድገትን የሚያመጡ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
የሕግና የፖሊሲ ማሻሻያዎች እንዲሁም የንግድና ኢንቨስትመንት ምህዳሩን የመክፈት እርምጃዎችም ትልቅ ውጤት እያመጡ ነው ብለዋል።
በተወሰዱ እርምጃዎች ኢኮኖሚው ከፍተኛ ዕድገት እያስመዘገበ መሆኑን ገልጸው፥ ኢትዮጵያ የፋይናስ ዘርፉን ጤናማነት በማረጋገጥ ለኢንቨስተሮች ምቹ አቅም መፍጠሯን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ወደ ስራ መግባቱም ተወዳዳሪ እና በግሉ ዘርፍ የሚመራ ኢኮኖሚ ለመገንባት ጉልህ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር) በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ሀገር ናት ብለዋል።
ከሀገራዊ ለውጡ በፊት የግሉ ዘርፍ ትኩረት ሳይሰጠው መቆየቱን ያወሱት ሚኒስትሩ፥ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የፖሊሲ ዕይታን በመቀየር የግሉ ዘርፍ ዋነኛ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ለበርካታ አስርት ዓመታት ለውጭ ባለሀብቶች ዝግ ሆነው የቆዩ ዘርፎች መከፈታቸውን በማንሳት፥ ለኢንቨስትመንት ምቹ ያልነበሩ ህግጋትና ፖሊሲዎች ተሻሽለዋል ነው ያሉት።
ኢትዮጵያ ታዳሽ ኃይልን በተመጣጣኝ ዋጋ የምታቀርብ ሀገር መሆኗን ጠቅሰው፥ ይህም ለኢንቨስተሮች ምቹ ሁኔታን የፈጠረ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር)፥ በለውጡ ዓመታት መንግስት ለኢንቨስትመንት ዘርፍ በሰጠው ትኩረት ከፍተኛ ውጤት መመዘገቡን ገልጸዋል።
ፎረሙ ትብብርን በማጠናከር የኢንቨስትመንት እድሎችን እንደሚያሰፋ ጠቁመዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025