አዲስ አበባ፤ ግንቦት 4/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የተገበረችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ዋነኛ ዓላማ ለውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ምቹና ተወዳዳሪ ምህዳር መፍጠር መሆኑን የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ገለጹ።
በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ 2025 የቢዝነስ ፎረም የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ፣ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮችና የበርካታ ሀገራት ኢንቨስተሮች በተገኙበት ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
በመድረኩ በኢትዮጵያ ባሉ መልካም የኢንቨስትመንት እድሎች ዙሪያ በመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ገለጻና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ የተሟላ ማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ዓላማ ኢንቨስትመንትን መደገፍ እንዲሁም ተወዳዳሪ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ምህዳርን መፍጠር ነው ብለዋል።
ይህም በውስጡ በርካታ ፕሮግራሞችን መያዙን ገልጸው የፕሮግራሙ ዋናው አካልም የገንዘብ ፖሊሲን ከማዘመን ጋር የተያያዘ መሆኑን ገልጸዋል።
ሪፎርሙ ተግዳሮቶችን በተሻለ ሁኔታ መፍታት የሚያስችል ሆኖ መዘጋጀቱንና ኢንቨስተሮችንም ገቢ ማመንጨት የሚያስችላቸው መሆኑን ተናግረዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ ግዙፍ የታዳሽ ኃይል ባለቤት መሆኗን በማንሳት፥ በቀጣናው ቁልፍ ተዋናይ ሆና መቀጠሏን ገልጸዋል።
ባለፉት ሰባት ዓመታት መንግስት ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እና ዘላቂ እድገት ለማምጣት ወሳኝ እርምጃዎችን መውሰዱን ተናግረዋል።
በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በማዕድን፣ በቱሪዝም እና በዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ እድሎችን ማስፋትን የሚያካትቱ ቁልፍ ተግባራት መከናወናቸውን ጠቅሰዋል።
የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) ኢትዮጵያ ለአስርት ዓመታት ጦም ያደረ መሬትን ሙሉ በሙሉ ወደ እርሻ እያስገባች እንዲሁም አዳዲስ የማዕድን ዕድሎችን እየተመለከተች መሆኗን ጠቁመዋል።
በርካታ የኢንቨስትመንት እድሎችን የሚያሰፉ ማሻሻያዎች መደረጋቸውንና ከዚህም ጀርባ የመንግስት ከፍተኛ ቁርጠኝነት መኖሩን አመላክተዋል።
የፍትሕ ሚኒስትር ሀና አርዓያሥላሴ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በአብዛኛው ለውጭ ባለሀብቶች ዝግ ሆኖ መቆየቱን አውስተዋል።
ባለፉት የለውጥ ዓመታት በርካታ አዳዲስ አሰራሮችን በመዘርጋት ወሳኝ እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል።
በተሻሻለው የኢንቨስትመንት ህግም በርካታ ዘርፎች ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት መደረጋቸውን ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025