
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2017(ኢዜአ)፦ ዲጂታል ቴክኖሎጂ የአገልግሎት አሰጣጥን በማቀላጠፍ የገቢ አቅምን ለማሳደግ ገንቢ ሚና እየተጫወተ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።
ተቋማት ዲጂታል ቴክኖሎጂን ገንብተው አገልግሎት አሰጣጣቸውን እንዲያቀላጥፉ መንግስት በርካታ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል፡፡
በዚህም በርካታ ተቋማት ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ለህብረተሰቡ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
ከእነዚህ ተቋማት መካከል የገቢዎች ሚኒስቴርን ለአብነት ማንሳት ይቻላል።
በገቢዎች ሚኒስቴር የመረጃ፣ ቴክኖሎጂ ልማትና አስተደዳር ዳይሬክተር ኩራቱ ለማ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ሚኒስቴሩ የገቢ ግብር አሰባሰብ አቅምን የሚያሳድጉ የቴክኖሎጂ አሰራር ሥርዓቶች ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል።
ይህም በዘርፉ አገልግሎት አሰጣጡን በማቀላጠፍ ውጤቶች እንዲመዘገቡ እያስቻለ ይገኛል ብለዋል፡፡
የቴክኖሎጂና የኤሌክትሮኒክስ የገቢ ግብር ሥርዓቶች ተግበራዊ መደረግ ህገ-ወጥ ዝንባሌዎችን በመከላከል በኩል እያመጡ ያለውን ውጤት ለአብነት አንስተዋል።
ግብር ከፋዩ ባለበት ቦታ ሆኖ ክፍያ መፈጸም የሚችልበት ምቹ አጋጣሚ መፍጠሩንም ጨምረው አንስተዋል።
ቴክኖሎጂው በአሁን ወቅት 95 በመቶ የፌደራል ግብር ከፋዮች ግብራቸውን በዘመናዊና መንገድ እንዲከፍሉ አስችሏል ብለዋል።
የገቢ አሰባሰብ ሂደቱን ሙሉ ለሙሉ በዘመናዊ የቴክኖሎጂ ሥርዓት ለማከናወን ከባለድርሻ አካላትና ቴክኖሎጂ አልሚዎች ጋር በትብብር እየተሰራ እንደሚገኝም አስረድተዋል።
ኢዜአ ያነጋገራቸው ግብር ከፋዮች በበኩላቸው ቀደም ሲል የነበረው የግብር አሰባሰብ ሂደት በተለይ ለግብር ከፋዩ የተቀላጠፈ እንዳልነበር ተናግረዋል።
አቶ አሸናፊ አለሙ ቀደም ሲል የነበረው የግብር አሰባሰብ ሂደት በንግዱ ዘርፍ ለመሰማራት የማይጋብዝና ለእንግልትና ለወጪ የሚዳርግ እንደነበር አስታውሰዋል።
አሁን ላይ ግብርን በዘመናዊ መንገድ መክፈል የሚቻልበት አሰራር በመተግበሩ በቀላሉ መክፈል እንዳስቻላቸው ገልጸዋል።
ሌላው ግብር ከፋይ አቶ አለማየሁ ተክለማሪያም በበኩላቸው፤ የግብር አሰባሰብ ስርዓት ወደ ዘመናዊ መምጣቱ ግብር ከፋዩን የሚያነቃቃ ነው ብለዋል።
የግብር አከፋፈል ሂደቱ ፈጣንና ጊዜውን የዋጀ እንዲሆን ተደርጓል ያሉት ደግሞ ሌላኛው አስተያያት ሰጪ ፍቃዱ ድሪባ(ዶ/ር) ናቸው።
በመሆኑም ግብር ከፋዩ ግብሩን ወቅቱን ጠብቆ እንዲከፍል ማስቻሉን ተናግረዋል።
ጅማ፤ ሚያዝያ 16/2018 (ኢዜአ)፡- በጅማ ዞን ባለፉት ዘጠኝ ወራት 52 ሺህ ቶን ቡና ለገበያ መቅረቡን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ቲጃኒ ተማም ተናገሩ...
Apr 24, 2026
ጅግጅጋ፤ ሚያዝያ 13/2018 (ኢዜአ)፦ የኅብረት ሥራ ማኅበራትን በቴክኖሎጂና ሌሎች መስኮች የማጠናከር ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሠ መ...
Apr 22, 2026
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 6/2018(ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በስንዴ ልማት ያስመዘገበችው ስኬት ለአፍሪካዊያን በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን የአ...
Apr 15, 2026
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026