
ሀዋሳ፤ ግንቦት 6/2017(ኢዜአ)፦ አርሶ አደሮች ምርቶቻቸውን በበለጠ ጥራትና ብዛት ለኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዲያቀርቡ በማስቻል የተሻለ ገቢ እንዲያገኙ እንደሚሰራ የሲዳማ ክልል ኢንዱስረትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ።
ኮርፖሬሽኑ ከይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ኢንዱስረትሪ ፓርክ ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡
የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊና የኮርፖሬሽኑ የቦርድ ሰብሳቢ አራርሶ ገረመው(ዶ/ር) አርሶ አደሮች ምርቶቻቸውን በበለጠ ጥራትና ብዛት ለኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዲያቀርቡ በማስቻል የተሻለ ገቢ እንዲያገኙ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
ለፓርኩ የተለያዩ የግብርና ምርቶችን በግብዓትነት የሚያቀርቡ አርሶ አደሮች ትስስር በማጠናከር ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ ትኩረት ተደርጓል ብለዋል።

በእስካሁኑ ሂደት ከፓርኩ ጋር ትስስር የተፈጠረላቸው አርሶ አደሮች ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቅሰው ምርቶቻቸውን በበለጠ ጥራትና ብዛት በማቅረብ የተሻለ ገቢ ማግኘት እንዲችሉ ይደረጋል ብለዋል፡፡
በቀጣይ ሶስት ወራት ከፓርኩ ጋር ትስስር የተፈጠረላቸው 40ሺህ አርሶ አደሮች የምርቶቻቸውን ጥራትና ብዛት ማሳደግ የሚያስችላቸውን ሥልጠና እንደሚሰጣቸው ገልጸዋል።
ሥልጠናው በምርት ሂደት፣ በአሰባሰብና አያያዝ ላይ የዘመነ አሰራር እንዲከተሉ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያለመ መሆኑንም ተናግረዋል።

የክልሉ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኃይሉ ዬቴራ፤ ፓርኩ ሥራ ከጀመረ አንስቶ በግብዓት ትስስርና በሥራ ዕድል ፈጠራ አርሶ አደሮችንና ወጣቶችን ተጠቃሚ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰዋል።
ከሶስት ዓመት በፊት በፓርኩ የግብዓት ሰንሰለት ውስጥ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ትስስር የተፈጠረላቸው አርሶ አደሮች 36ሺህ እንደነበሩ ጠቅሰው በአሁን ወቅት ቁጥራቸውን 136ሺህ መድረሱን ተናግረዋል፡፡
በአሁን ወቅት በፓርኩ አቮካዶ፣ ወተት፣ ማርና ቡና የሚያቀነባብሩ ስምንት ኩባንያዎች በሥራ ላይ መሆናቸውን አንስተው ግብዓት የሚያቀርቡ አርሶ አደሮች ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የተሻለ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሥልጠናው እንደሚያግዛቸው አስረድተዋል፡፡
በምክክር መድረኩ የክልል፣ የዞን እና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም የኮርፖሬሽኑ፣ የኢንዱስትሪ ፓርኩና የኩባንያ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ሰኔ 2 /2018 (ኢዜአ)፦የዕቃ ማከማቻ ደረሰኝ ሥርዓት ደንብ የግብርና ኢኮኖሚ ሽግግርን በማሳለጥና የገጠር ልማትን በማጎልበት አርሶ አደሮችን ተጠ...
Jun 10, 2026
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 1/2018 (ኢዜአ)፦ በመዲናዋ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን በማላቅ የተገልጋዮችን እርካታ የሚያሳድጉ ሰው ተኮር ተግባራት ተጠናክረው እንደ...
Jun 9, 2026
ሀዋሳ ፤ ግንቦት 28/2018 (ኢዜአ) ፦በይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ማቀነባበሪያ ፓርክ ከአምራች ኢንዲስትሪዎች ጋር በተፈጠረላቸው የገበያ ትስስር ...
Jun 6, 2026
ነገሌ ቦረና፤ ግንቦት 19/2018(ኢዜአ)፦ የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት መጀመር የአካባቢውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የበለጠ የሚያ...
May 28, 2026