
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 7/2017(ኢዜአ)፦ በቤተሰብ ደረጃ ኢኮኖሚን በማሳደግ ወደ ተሻለ ተጠቃሚነት ለማሸጋገር ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸው የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስገነዘበ።
የቤተሰብ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ32ኛ ጊዜ በኢትየጵያ ደግሞ ለሶስተኛ ጊዜ "የተሻሻለ የቤተሰብ ሥራና ገቢ ለሀገር ኢኮኖሚ" በሚል መሪ ሀሳብ ተከብሯል።
የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የቤተሰብ ኢኮኖሚ አቅምን ማሻሻል እና ጥሪት ግንባታን መደገፍ ይገባል።
በተለይም የፌዴራልና የክልል አስፈጻሚ አካላት የቤተሰብ የክህሎት ክፍተትን በመሙላት፣ የመስሪያ ቦታ እና የፋይናንስ አቅርቦት ችግር ለማቃለል በቁርጠኝነት እንዲሰሩም ጠይቀዋል።
በሀገሪቱ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል አንዱ የቤተሰብ ደህንነት ጥበቃ እና ጥሪት ግንባታ በመሆኑ በዘርፉ ለውጥ ለማምጣት ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።
ማንኛውም ቤተሰብ በሀገራዊ ብልጽግና እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ውስጥ አዎንታዊ ሚና እንዲኖረው ሁኔታዎችን ማመቻቸት እንደሚገባም ነው የጠቆሙት።
ቤተሰብን ከድህነትና ከተረጂነት በማላቀቅ ወደ ምርታማነት እና የተሻለ ተጠቃሚነት ለማሸጋገር ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸው አንስተዋል።
ቤተሰብ በተነቃቃ የስራ ባህል ጥሪት በማፍራት፣ ኢኮኖሚውን በመገንባትና ለቀጣዩ ትውልድ ጭምር በማሸጋገር ለማህበረሰብ ሁለንተናዊ ለውጥ የጎላ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም ተናግረዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026