
ጅማ፤ ግንቦት 11/2017(ኢዜአ)፡- የራስን አቅም በማጎልበትና ምርታማነትን ይበልጥ በማሳደግ የምግብ ሉአላዊነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ገለጹ።

የክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የዓመቱ የሌማት ትሩፋት መርሃግብር፣ የስነ ምግብና የሰቆጣ ቃልኪዳን ስራዎችን በመገምገም አቅጣጫ የሚያስቀምጥ መድረክ በጅማ ከተማ እየተካሄደ ነው።
አቶ አደም በወቅቱ ባደረጉት ንግግር፤ ያለንን ሰፊ ለም መሬት፣ የሰው ሀብት እና የውሃ ሀብት በመጠቀም የግብርና አቅማችንን በማጎልበት ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር በመሰራት ላይ ይገኛል ብለዋል።
የራስን አቅም አጎልብቶ ምርትና ምርታማነትን ይበልጥ በማሳደግ የምግብ ሉአላዊነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የተለያዩ የግብርና ኢንሼቲቮች ተቀርፀው ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን ጠቁመው፤ ይህም በስንዴ፣ በሩዝ፣ በማር እና በሌሎችም የግብርና ዘርፎች ያተኮሩ መሆኑን ገልጸዋል።
በመድረኩ ላይ የፌደራል፣ የክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች ከፍተኛ የአመራር አባላት ተገኝተዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026