
ሰመራ፤ ግንቦት 12/2017 (ኢዜአ) ፡-የፋይዳ ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚ መሆናችን ፈጣንና ቀጣይነት ያለው አገልግሎት ማግኘት የሚያስችለን ነው ሲሉ በሠመራና አካባቢው የሚገኙ የመታወቂያው ተመዝጋቢዎች ተናገሩ።
በሠመራ ከተማ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ መዝገባ በንቅናቄ መልክ በመከናወን ላይ ይገኛል።
በምዝገባ ሂደት ላይ ኢዜአ ካነጋገራቸው ተመዝጋቢዎች መካከል የዱብቲ ከተማ ነዋሪ አቶ ሳኒ አህመድ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚሰሩ የማጭበርበር ወንጀሎችን ለመከላከል ጥቅሙ የጎላ ነው ብለዋል ።

ሌላዋ የሠመራ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ ሶፊያ አደም በበኩላቸው የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ባለቤት መሆን ጥቅሙ ብዙ መሆኑን በመረዳታቸው ለመመዝገብ መምጣታቸውን አብራርተዋል።

የፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ማግኘታችው እንደፈለጉ ተንቀሳቅሰው ለመስራትና ቀልጣፋ አገልግሎት ለማግኘት እንደሚረዳቸው የገለጹት ደግሞ የዱብቲ ከተማ ነዋሪ አቶ ማህሙድ ዓሊ ናቸው።

"ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎቶችን በአንድ ላይ ለማግኘት የሚያችለን ነው" ያሉት ደግሞ የሠመራ ከተማ ነዋሪ አቶ ሁሴን መሐመድ ናቸው።

በኢትዮ ቴሌኮም የሰሜን ምስራቅ ምስራቅ ሰመራ ሪጅን የሽያጭ ክፍል ኀላፊ አቶ ሃጎስ ወልደጊዮርስ በበኩላቸው ፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ የኢትዮጵያን የዲጂታል አለምን ጉዞ የሚያሳልጥ ቁልፍ መሣሪያ ነው ብለዋል።

እንደ አገር እየተከናወነ ያለውን የዲታላይዜሽን ጉዞ ለማፋጠንና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚረዳ መሆኑን አብራርተዋል።
በዚህም አገልግሎቱ በተለያዩ ደረጃ የሚከናወኑ ማጭበርበሮችን የሚከላከል በመሆኑ በክልሉ የተለያዩ ማዕከሎች እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026