
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዲጂታል ኢኮኖሚ ለምታደርገው ንቁ ተሳትፎ ፋይዳ ወሳኝ ሚና እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ዲጂታል ማንነት ላይ ትኩረቱን ያደረገው አይዲ ፎር አፍሪካ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ዲጂታል ማንነትን ማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያድርግ ዘመናዊ፣ አካታች እና መሠረታዊ የዲጂታል ማንነት መለያ ስርዓት መዘረጋቷን ጠቁመዋል።
ፋይዳ ካርድ ብቻ ሳይሆን ልዩ የሆኑ ቁጥሮችን የያዘና ማንነት የሚረጋገጥበት መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እስካሁን ለ15 ሚሊዮን ዜጎች ተደራሽ መደረጉን ጠቁመዋል፡፡
ዜጎች በዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ፋይዳ ትልቅ ዕድል መፍጠሩን ገልጸው፤ ለሁሉም ዘርፎች ምቹ መደላደል ማድረጉንም ጠቁመዋል፡፡
ፋይዳን ለፋይናንስ፣ ጤና፣ ትምህርት፣ ቴሌኮም፣ የህዝብ አገልግሎቶች ከማህበራዊ ዋስትና ጋር በማስተሳሰር ተዓማኒ የሆነ መደላድል ለህዝቡ ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
ፋይዳ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ፈጣን የሆነ ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት ትልቅ አበርክቶ እንዳለው ጠቁመው፤ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና እውን ለማድረግ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወትም ተናግረዋል፡፡
የዲጂታል ማንነት መለያ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ወሳኝ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለዓላማው በህብረት በመሰለፍ የአፍሪካን እምቅ አቅም ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከኮንፈረንስ ማዕከልነት ባሻገር የራሷ ማንነት ያላት ናት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እጅግ ውብ በሆኑ የአዲስ አበባ ጎዳናዎች እንዲሁም ከመልክዓ ምድሯ ልምድ መውሰድ የሚቻል ስለመሆኑም አንስተዋል፡፡
ተሳታፊዎች ወደ መጡበት አካባቢ ሲመለሱም ሁሉም ሰው አስተማማኝ የዲጂታል ማንነት መለያ እንዲኖረው በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባም አመልክተዋል፡፡
በመድረኩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አገኘው ተሻገር፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮችና የአለም አቀፍ ድርጅት ተወካዮች ታድመዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026