አዲስ አበባ፤ ግንቦት 14/2017(ኢዜአ)፦በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፉ የተጀመሩ የዲጂታላይዜሽን ሥራዎች ተጨባጭ ለውጥ እያመጡ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ገለጹ።
“በዲጂታል የታገዘ ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ” በሚል መሪ ሀሳብ የመንግስት ተቋማት ተወካዮችን፣ የልማት አጋሮችን፣ የኢንዱስትሪ መሪዎችን እና ባለሙያዎችን የተሳተፉበት አውደ ጥናት ተካሂዷል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) እንደገለጹት፥ በዲጅታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ተጨባጭ ለውጥ ከመጣባቸው ዘርፎች ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አንዱ ነው።
ዘርፉን በዲጂታል ለማዘመን ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን በመጥቀስ፥ በመንግሥትና በግል አጋርነት የትራንስፖርት አገልግሎትን የሚያሳልጡ ቴክኖሎጂዎች መተግበራቸውን ተናግረዋል።
የዲጂታል ትራንስፖርት ማዕቀፍ፣ ስማርት መሰረተ ልማት፣ ዲጂታል የነዳጅ የክፍያ ስርዓት፣ ዲጂታል የትኬት መቁረጫና የክፍያ ዘዴ፣ ስማርት የመኪና ማቆሚያዎችና ዲጂታል የትራፊክ አስተዳደር ስርዓት መዘርጋታቸውን አንስተዋል።
በስትራቴጂክ ሪፎርም የተደገፉ አገልግሎትን የማዘመንና የማሻሻል ስራዎች የዘርፉን አጠቃላይ እንቅስቃሴና እድገት እየቀየሩት ነው ብለዋል።
የዲጂታል ክህሎት፣ መሰረተ ልማት፣ የሳይበር ደህንነትና ሌሎች ተግባራትን አጠናክሮ ለመጠቀልም የመንግሥትና የግሉ አጋርነት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል።
ዲጂታል ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ወደ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ለሚደረገው ሽግግር ወሳኝ በመሆናቸው የቅንጅት ስራዎች ሊጠናከሩ እንደሚገባም ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
የአይሲቲና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ይልቃል አባተ፥ በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ የተሰማሩ የግል ተቋማትና ባለድርሻ አካላት አገልግሎታቸውን ለማሻሻል የዲጅታል አሰራርን ማጠናከር አለባቸው ብለዋል።
የራይድ መስራችና ስራ አስፈጻሚ ሳምራዊት ፍቅሩ በበኩላቸው፥ በትራንስፖርት ዘርፉ ዲጂታላይዜሽንን የሚደግፉ ምቹ ሁኔታዎች መፈጠራቸውን ገልፀዋል።
የዘርፉን አገልግሎት ይበልጥ ለማዘመንና የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት የመንግስትና የግል አጋርነት ሊጠናከር እንደሚገባም ጠቁመዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025