የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከጎረቤት አገሮች ጋር የጋራ ልማትና ትስስርን አጠናክሯል

May 26, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ግንቦት 16/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከጎረቤት አገሮች ጋር የጋራ ልማትና ትስስርን ማጠናከሩን ተገለጸ።


በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዳሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሽብሩ ማሞ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በዲፕሎማሲው መስክ በዓለም አቀፍ መድረክ እውቅና እና ተቀባይነት ያገኘ መሆኑን አስረድተዋል።


የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ለጎረቤት አገሮች ቅድሚያ የሚሰጥ እንደመሆኑ የጋራ ተጠቃሚነትና ቀጣናዊ ትስስርን የበለጠ ለማጠናከር በመሰረተ ልማት፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ በትብብር እየሰራች እንደምትገኝ ተናግረዋል።


በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጭነት ከስድስት ዓመት በፊት በተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከጎረቤት አገሮች ጋር በቅርበት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።


ኢትዮጵያ ከራሷ አልፋ ለጎረቤት አገሮች ችግኝ በመስጠት፣ በመትከልና ልምድ በማካፈል ትስስርን ለማጠናከር ከሰራችው ጠንካራ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ስራዎች ውስጥ ተጠቃሽ መሆኑን ጠቅሰዋል።


በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከጎረቤት አገሮች ጋር አብሮ የመልማት፣ የመበልጸግ፣ የተፈጥሮ ሃብትን በዘላቂነት በመጠበቅ በፍትሃዊነት የመጠቀም አቋሟን ያጠናከረችበትና በተሞክሮነት የተወሰደ መሆኑን ገልጸዋል።


የአየር ንብረት ለውጥን በዘላቂነት ለመከላከልና የተፈጥሮ ሃብትን ለመጠበቅ በመርሃ ግብሩ ያስመዘገበቻቸውን ውጤቶች በዓለም አቀፍ መድረኮች ልምዷን ማካፈሏንም ነው አምባሳደር ሽብሩ የገለጹት።


በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን በመትከል ያስመዘገበችው አስደናቂ ውጤት በዓለም አቀፍ መድረክ እውቅናን እንዳገኘ አስታውሰዋል።


በተለያየ የዓለም አገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች መርሃ ግብሩን የበለጠ ለማስፋትና ለማስተዋወቅ በትኩረት እየሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል።


የጎረቤት አገሮች ከኢትዮጵያ ልምድ በመውሰድ ችግኝ እንዲተክሉ መነሳሳትን የፈጠረ በጎ ተጽዕኖ መፍጠሩን ገልጸዋል።


በግብርና ሚኒስቴር የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም መሪ ስራ አስፈጻሚ ፋኖሴ መኮንን በበኩላቸው፥ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተጎዳ መሬት እንዲያገግም፣ የመሬት እርጥበታማነት እንዲጨምር፣ የውሃ አካላት በመጠን እንዲጨምር ማድረጉን ዘርዝረዋል።


እንደ መሪ ስራ አስፈጻሚው ገለጻ፥በመርሃ ግብሩ 40 በመቶ የደንና 60 በመቶ የፍራፍሬ፣የእንስሳት መኖ፣ የአፈር ለምነትና ጤንነትን የሚጠብቁ ችግኞችን በመትከል ተጨባጭ ውጤት ተመዝግቧል።


ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃና እንክብካቤ ልምድ በማካፈል ከጎረቤት አገሮች ጋር በትብብር የመልማት ጽኑ ፍላጎቷን ያሳየችበት እንደሆነም ተናግረዋል።


በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የሚተከሉ ችግኞች የታችኞቹ ተፋሰስ አገራት በጎርፍ አደጋ እንዳይጠቁ የራሱን አስተዋጽኦ እያደረገ እንደሚገኝም ተናግረዋል።


ለ2017 የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከሰባት ነጥብ አምስት ቢሊዮን በላይ ችግኝ ዝግጅት መደረጉን አቶ ፋኖሴ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ ነው</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...

Feb 28, 2025

<p>በዞኑ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ ነው</p>

ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...

Feb 24, 2025

<p>የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተደረገ ነው - ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል</p>

አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...

Feb 24, 2025

<p>ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች ነው -የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...

Feb 12, 2025