አምቦ፤ግንቦት 16/2017(ኢዜአ)፦በአምቦ ከተማ በ2017 በጀት ዓመት ከ3 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እየተገነቡ የሚገኙ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገለጸ።
የአምቦ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ተስፋዬ ደገፋ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ በበጀት ዓመቱ በከተማው የህዝቡን የልማት ጥያቄ የሚመልሱ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች እየተሰሩ ነው።
በከተማዋ እየተከናወኑ ካሉት የመሰረተ ልማት ግንባታዎች መካከል 28 ኪሎ ሜትር መንገድ፣የመንገድ ዳር መብራት፣የፍሳሽ ማስወገጃ ቦይ፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ፣ የኮሪደር ልማት ስራዎች እና ሌሎችም ይገኙበታል ብለዋል።
ከተማዋን አቋርጦ የሚያልፈው መንገድ ጠባብ በመሆኑ በከተማዋ የትራፊክ ፍሰት ላይ ጫና ሲያደርግ መቆየቱን ገልጸው፥ ችግሩን ለመፍታትም ዋናውን መንገድ የማስፋት እና የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በከተማው በከብት ማደለብ፤ በዶሮ እርባታ፣ በወተት ላምና በዓሳ እርባታ እንዲሁም በሌሎች የኢኒሼቲቭ ስራዎች ለተሰማሩ አካላት የሼድ ግንባታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በከተማዋ ያለው የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ሽፋን እስካሁን 90 በመቶ መድረሱን አንስተው፥ የከተማዋ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ደግሞ 89 በመቶ መሆኑን አስረድተዋል።
በከተማው እየተገነቡ ያሉት መሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች እስካሁን ከ9 ሺህ 300 ለሚበልጡ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን አመልክተዋል።
እየተከናወነ በሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራም የመንገድ ዳር ማስዋብ፣ የፍሳሽ ማስወገጃ ቦይ፣የተለያዩ አደባባዮችን ጨምሮ መዝናኛ ቦታዎች እና ሌሎች የልማት ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።
በከተማው በሰፈነው ሰላም በሃገር ውስጥና በውጭ ያሉ ባለሃብቶች ወደ ከተማው መጥተው ኢንቨስት እንዲያርጉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የአምቦ ከተማ ነዋሪ ወጣት አበበ ገመቹ በበኩሉ፥ በከተማው አስተዳደር እና በሕብረተሰቡ ተሳትፎ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች ህዝቡን ተጠቃሚ እያደረጉ በመሆናቸው የድርሻውን እንደሚወጣም ተናግሯል፡፡
ሌላኛው የከተማው ነዋሪ አቶ ባይሳ ተሾመ በበኩሉ፥ ከለውጡ ወዲህ የአምቦ ከተማ ህዝብ ጥያቄ ተራ በተራ እየተመለሰ ስለሆነ ህብረተሰቡም የተለመደ ትብብሩን እያደረገ ነው ብለዋል።
የከተማው ኮሪደር ልማት ከሌሎች በክልሉ ከሚገኙ ከተሞች አንፃር ሲታይ ቀሪ ስራዎች ቢኖሩም የተጀመሩ ተግባራት ግን አበረታች መሆናቸውን የገለፁት ደግሞ ሌላኛዋ የከተማዋ ነዋሪ ወይዘሮ ብልብሉ በሪሶ ናቸው።
ሕብረተሰቡ እያደረገ ያለው ድጋፍ ለሌሎች ምሳሌ ሊሆን እንደሚችል ገልፀው እርሳቸውም የድርሻቸውን እንደሚወጡም ተናግረዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025