አዲስ አበባ፤ግንቦት 16/2017(ኢዜአ)፦ የብራዚል አፍሪካ የግብርና ዘርፍ ጉባኤ ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ከብራዚል ጋር ያላትን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ያስቻለ መሆኑን በብራዚል የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ ገለፁ።
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስን ጥሩነህ የተመራ ልዑክ በምግብ ዋስትና፣ ረሃብን በመዋጋት እና በገጠር ልማት አጀንዳዎች ላይ ባተኮረው ሁለተኛው የብራዚልና አፍሪካ ጉባኤ ላይ የተሳተፈ ሲሆን በብራዚልም ጉብኝቶችን አድርጓል።
የልዑኩን ቆይታ አስመልክቶ በብራዚል የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸውም ልዑክ ቡድኑ የብራዚል አፍሪካ የግብርና ዘርፍ ላይ ያተኮረ ጉባኤ ላይ መሳተፉን ተናግረዋል።
ከጉባኤው ጎን ለጎን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከብራዚል ምክትል ፕሬዝዳንት ጋር ግብርናን ጨምሮ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በቱሪዝም እና በአቪዬሽን ዘርፍ ያሉትን ግንኙነት ማሳደግ የሚያስችል ውይይት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።
ጉባኤው ብራዚልና አፍሪካ በግብርናው ዘርፍ በጋራ ለመስራት ልምድ በመለዋወጥ ረገድ እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ያተኮረ ስኬታማ መሆኑን ተረናግረዋል።
ከጉባኤው ጎን ለጎን የሀገሪቱን የግብርና ዘርፍ ተግባራት የመስክ ምልከታ መደረጉን ገልጸው፤ በዚህም ልምድ የተወሰደበት መሆኑን አምባሳደሩ አንስተዋል።
በርካታ ተሞክሮዎች የተገኙበት መሆኑን ም ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያ ከብራዚል ጋር ያላትን የግብርና ዘርፍ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ የሚያስችል እንደሆነ አስረድተዋል።
በጉባኤው ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ያስመዘገበቻቸውን ስኬቶች ለአፍሪካ ሀገራት እና ለብራዚል ማጋራቷን አምባሳደሩ ገልፀዋል።
በአረንጓዴ ልማት፣ በሌማት ትሩፋት፣ በስንዴ ምርትና ምርታማነት የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማጋራት መቻሉንም ጠቅሰዋል።
በግብርና ዘርፍ ያለውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል የሁለትዮሽ የግብርና ትብብር ስምምነት መፈረሙንም አንስተዋል።
ጉባኤው እና ጉብኝቱ ለሀገራችን ግብርና ዘርፍ ተሞክሮ የተወሰደበት በተለይ ግብርና በቴክኖሎጂ ሲታገዝ የላቀ ለውጥ እንደሚያመጣ መገንዘብ የታቸለበት ነው ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025