ሮቤ ፤ግንቦት 16/2017(ኢዜአ) ፡-በኦሮሚያ ክልል የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ የሚያስችሉ የግንባታ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸው ተገለጸ።
በብልጽግና ፓርቲ ኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ መንግሥቱ በቀለ (ዶ/ር)ን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች በሮቤ ከተማ አስተዳደር እየተገነቡ የሚገኙ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።
ኃላፊው መንግሥቱ በቀለ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደተናገሩት፤ የክልሉ መንግሥት የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄዎች የሚመልሱና ተጠቃሚነቱን ለሚያረጋግጡ የግንባታ ፕሮጀክቶች ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው።
በተለይ የህዝቡን የመልማት ፍላጎት ታሳቢ ያደረጉና ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ የልማት ፕሮጀክቶች ተጠናክረው መቀጠላቸውን አመልክተዋል።
በሮቤ ከተማ አስተዳደር እየተገነቡ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶችና ኢኒሼቲቮች የጥረቱ ማሳያዎችና ለብልጽግና ጉዞ ስኬት የላቀ ድርሻ ያላቸው መሆኑን አመልክተዋል።
የሮቤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዲኖ አሚን በበኩላቸው፥አስተዳደሩ ከተማውን ለነዋሪው ምቹ የመኖሪያ ቦታና የቱሪዝምና ንግድ ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ ነው።
አስተዳደሩ በበጀት ዓመቱ የከተማዋን የንግድ ማዕከልነት ይበልጥ የሚያሳድጉ ከ60 በላይ ፕሮጀክቶች በግንባታ ሂደት ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።
የከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጉብኝትም በዘርፉ የሚታዩ መልካም አጋጣሚዎችና የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች እንዲፈቱ አቅም እንደሚፈጥር አመልክተዋል።
በአመራሮቹ ከተጎበኙ የልማት ፕሮጄክቶች መካከል የ''ሎላ ሻያ'' የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክት፣የንብ ማነብና ዶሮ እርባታ ማዕከል ግንባታን ጨምሮ ሌሎች በከተማ አስተዳደሩ እየተከናወኑ የሚገኙ ኢኒሼቲቮች ተጎብኝቷል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025