
አዲስ አበባ፤ግንቦት 18 /2017(ኢዜአ)፦የሎጂስቲክስ ዘርፉ ቀልጣፋና ተደራሽ በማድረግ የወጪና ገቢ ንግድ እንቅስቃሴን ውጤታማ ለማድረግ የባለ ድርሻ አካላት ሚና የላቀ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ ከከባድ መኪና አሽከርካሪዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር የጭነት ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ አገልግሎትን የበለጠ ማቀላጠፍ በሚያስችል ጉዳይ ላይ በሞጆ ደረቅ ወደብ የምክክር መድረክ አካሂዷል።

መድረኩ የሎጂስቲክስ ስርዓቱን ቀልጣፋ እና ተደራሽ በማድረግ የገቢና ወጪ ንግድ እንቅስቃሴን ለማሳለጥ የባለድርሻ አካላትን ሚና ለማጎልበት የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታው ዴንጌ ቦሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
የሎጂስቲክስ ዘርፉን ቀልጣፋና ተደራሽ በማድረግ የወጪና ገቢ ንግድ እንቅስቃሴን ውጤታማ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ሚና የላቀ ነው።
ለዚህም ግንባር ቀደም ሚና የሚጫወቱት የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች መሆናቸው ነው ያነሱት።
የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ምርትንና አገልግሎትን ከቦታ ወደ ቦታ በማጓጓዝ በወቅቱ ለገበያ እንዲቀርብ በማድረግ በኩል ያላቸው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
በኢትዮጵያ ብሎም በሌሎች የአለም ሀገራት የሎጂስቲክስ ስርአት መቀላጠፍ የኢኮኖሚ እድገትን ለማፍጠን ትልቁን ድርሻ እንደሚይዝ ሚኒስትር ዴኤታው አክለዋል።
በኢትዮጵያ በተለይም የገቢና ወጪ ጭነት እንቅስቃሴ ውስጥ 86 በመቶ የሚሆነው በከባድ መኪኖች እንደሚጓጓዝ ገልፀዋል።
በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሎጂስቲክስ ዘርፍ አማካሪ መንግስቴ ሃይለማርያም (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ አሽከርካሪዎች የትራንስፖርት ዘርፉ ቀልጣፋና አስተማማኝ ብሎም ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ድርሻቸው የላቀ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በተለይም ድንበር ተሻጋሪ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች የሎጂስቲክስ ዘርፉን ለማሻሻል በሚደረገው እንቅስቃሴ የራሳቸው ሚና እንዲጫወቱ መሰል መድረኮች መዘጋጀታቸው ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ነው ያነሱት።
በኢትዮጵያ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር አስተባባሪና እና የተሽከርካሪ ባለቤት አቶ ቴድሮስ ሲሳይ በሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ አሽከርካሪዎች ሚናቸውን በአግባቡ እንዲወጡ መሰል መድረኮች መዘጋጀታቸው አበረታች ነው ይላሉ።
በዘርፉ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የሚያስችል አቅጣጫ ለማስቀመጥ አይነተኛ ሚና እንዳላቸው ጠቅሰዋል።
እንደዘርፉ ተዋናይም የሎጂስቲክስ ዘርፉን ቀልጣፋና ተደራሽ በማድረግ የወጪና ገቢ ንግድ እንቅስቃሴን ውጤታማ እንዲሆን የድርሻቸውን እንደሚወጡ ነው የተናገሩት።
ሌላኛው የከባድ መኪና አሽከርካሪ አቶ ፀጋዬ ጉታ በበኩላቸው፥ መድረኩ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ያላቸውን ጠንካራ ጎን አጠናክረው እንዲቀጥሉና ክፍተታቸውን እንዲሞሉ የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026