አዳማ፤ግንቦት19/2017 (ኢዜአ)፦ከእንስሳት ሀብት ልማት የሚገኘውን ጥቅም ለማሳደግ የሚያግዙ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ ከአለም አቀፍ የእንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን ''የኢትዮጵያ እንስሳትና ዓሳ ሀብት ኢንቨስትመንት ሰነድ''ለክልልና በየደረጃው ለሚገኙ ባለድርሻ አካላት ለማስተዋወቅ ያዘጋጀው መድረክ በአዳማ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ ላይ የግብርና ኢንቨስትመንትና ግብዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሶፍያ ካሳ (ዶ/ር) እንዳሉት፥ በአገራችን ካለው ሰፊ የእንስሳት ሃብት አኳያ በዘርፉ በሚፈለገው መጠን ጥቅም እየተገኘ አይደለም።
ሀገሪቷ ካላት አቅም አንፃር ወደ ውጪ ከሚላከው የእንስሳት ተዋፅኦ እየተገኘ ያለው 130 ሚሊዮን ዶላር አመታዊ ገቢ መሆኑን ጠቅሰው፥ ከዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም ለማሳደግ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጎልበት እንደሚጠይቅ አመልክተዋል።
በኢትዮጵያ የአለም አቀፉን መስፈርትና ደረጃን ያሟሉ 10 ቄራዎች ቢኖሩም በእንስሳት አቅርቦት ችግር ሳቢያ የሚጠበቀውን ያህል እየሰሩ አለመሆኑን ተናግረዋል።
በመሆኑም ሀገሪቷ ያላትን ሀብት ወደ ቄራዎቹ በማምጣት የተሻለ ጥቅምና የውጭ ምንዛሪ ግኝታችንን ይበልጥ ማስፋፋት ያስፈልጋል ብለዋል።
የሌማት ትሩፋት ከተጀመረ ወዲህ መነቃቃት እና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እየተገኘ ቢሆንም በእንስሳት ዘርፉ ከቦታ ልየታ አንስቶ የቴክኒክ ድጋፍ ውስንነቶች እንዳሉ አመላክተዋል።
የግሉ ባለሀብትም በዘርፉ ለመሰማራት ያሳየው ቁርጠኝነት አነስተኛ በመሆኑ ተሳትፎውን ሊያሳድግ እንደሚገባ ጠቁመው፥ ወጣቶችንም በዘርፉ በስፋት በማሳተፍ ለስራ እድልና ለውጭ ምንዛሪ ግኝት መጠናከር በቅንጅት መስራት ይገባል ብለዋል።
በዚህ ረገድም ሚኒስቴሩ የእንስሳት ሃብት ልማቱን ለማስፋፋትና ለማዘመን የሚያስችል ሰነድ ማዘጋጀቱን ጠቅሰው፥ ሰነዱ ሀገሪቷ በእንስሳት ዘርፍ ያላትን አማራጮች ያመላከተ መሆኑን ገልፀዋል።
በመሆኑም ሁሉም ክልሎች ካላቸው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር በመቃኘት ስራ ላይ ማዋል እንደሚገባቸውም አሳስበዋል።
በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሳ ልማት ዘርፍ አማካሪ አቶ ግርማ ሙሉጌታ በበኩላቸው፥ የእንስሳት እርባታ ዘርፍ ለስራ እድል ፈጠራ፣ የውጭ ምንዛሬ ገቢን ለማሳደግ፣ ለኢንዱስትሪ ጥሬ እቃነት ለማዋል በሚያስችል መልኩ እየተሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
የተዘጋጀው ሰነድም የኢንቨስትመንቱን እንቅስቃሴ በማነቃቃትና ኢትዮጵያን ከልማቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ድልድይ ሆኖ ያገለግላል ብለዋል።
በቀጣይም የእንስሳትና ዓሳ ንዑስ ዘርፎችን ወደ ዘመናዊ፣ተወዳዳሪ እና ለኤክስፖርት ብዝሃነት ቀጣይነት አይነተኛ መሳሪያነት ለመጠቀም ሁሉም ሊረባረብ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025