አዲስ አበባ፤ ግንቦት 19/2017(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሀገራት ለዘላቂ የውሃ ሀብት አስተዳደር እና ልማት ወጪ የሚያደርጉትን የኢንቨስትመንት መጠን እንዲያሳድጉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐመድ አሊ ዩሱፍ ጥሪ አቀረቡ።
ሶስተኛ የአፍሪካ የፓን አፍሪካ የውሃ ሀብት አስተዳደር ማዕቀፎች ትግበራ እና የአጋር አካላት ስብሰባ (PANAFCON3) ዛሬ በዛምቢያ ሉሳካ ተጀምሯል።
ስብሰባው እየተካሄደ የሚገኘው “የምንፈልጋትን አፍሪካ ለመፍጠር፤ ሁሉን አቀፍ እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የውሃ ደህንነት እና የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን ማረጋገጥ” በሚል መሪ ሀሳብ ነው።
በስብሰባው ላይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አመራሮች፣ የአባል ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮች፣ የአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት ተወካዮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
በስብሰባው የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍን ወክለው ንግግር ያደረጉት የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ብሉ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ ከባቢ አየር ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ ውሃ የአፍሪካ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚ ልማት የሚያሳልጥ ትልቅ አቅም መሆኑን አመልክተዋል።
አጀንዳ 2063ን ጨምሮ ሌሎች አህጉራዊ ግቦች ያለ ዘላቂ የውሃ ሀብት አቅርቦት እና አስተዳደር ሊሳኩ እንደማይችሉ ገልጸዋል።
የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ ለኢነርጂ ሽግግር፣ ለጤና አገልግሎት እና ኢንዱስትሪ ልማት የውሃ አቅርቦት እጅጉን አስፈላጊ እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ከዚህም አንጻር የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የውሃ እና የንጽህና አጠባበቅ ጉዳይን በመሪዎች ጉባኤ ላይ አጀንዳ እንዲሆኑና ሀገራት በብሄራዊ የልማት እቅዶቻቸው እንዲያካቱት የማድረግ ስራ እያከናወነ እንደሚገኝ አመልክተዋል።
ይህም በአፍሪካ የውሃ ሀብትን የማስተዳደር አካሄድ እንዲቀየርና ውሃ በሀገራት ዘንድ ያለው ዋጋ እና ግምት እያደገ መምጣቱን ነው ኮሚሽነሩ የገለጹት።
ኮሚሽነሩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ለውሃ ሀብት አስተዳደር እና ልማት የሰጡትን ትኩረት አድንቀዋል።
ይሁንና አፍሪካ እምቅ የሆነ የውሃ ሀብት ቢኖራትም አሁንም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ደህነቱ የተጠበቀ የውሃ አቅርቦት እንደማያገኙ እና በማህበረሰብ ጤና ላይ ችግሮች እንዳሉ አንስተዋል።
የአፍሪካ ሀገራት የዜጎች የውሃ አቅርቦትን ማሳደግ፣ በዘላቂ የውሃ ሀብት አስተዳደር ላይ የሚያፈሱትን መዋዕለ ንዋይ መጨመር፣ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓትን ማሳደግ እና የውሃ መሰረተ ልማት ግንባታን ማስፋፋት እንደሚገባቸው ነው ያስገነዘቡት።
በተለይም ሀገራት ብሄራዊ የውሃ ሀብት ኢንቨስትመንት ፕሮግራሞችን በመተግበር በውሃ እና ንጽህና አጠባበቅ ስራዎች ያሉ የኢንቨስትመንት ክፍተቶችን መሙላት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
የአፍሪካ ህብረት ከአጋር አካላት ጋር በመሆን ለሀገራት ሁሉን አቀፍ የውሃ አቅርቦት እንዲያረጋገጡና የንጹሃ መጠጥ ውሃ ተደራሽነትን እንዲያሰፉ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
አህጉራዊው ስብሰባ እስከ ግንቦት 21 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚቆይ ኢዜአ ከህብረቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025