ጋምቤላ፤ግንቦት 21/2017(ኢዜአ)፡-በጋምቤላ ክልል ያለው ሰፊ የዓሳ ሀብት በቴክኖሎጂ ታግዞ በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል የተጀመረው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ (ዶ/ር) በጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት የተገነባውን ዘመናዊ ዲጂታል ስማርት የኮሙኒኬሽን ማሳለጫ ክፍል ስራ በማስጀመር በክልሉ ዓሳ ሀብት ልማት ዙሪያ ከክልሉ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።
በዚህ ወቅት ሚኒስትር ዴኤታው፥በክልሉ ያለው እምቅ የዓሳ ሀብት በቴክኖሎጂ ታግዞ የሚፈለገውን ጥቅም እንዲያስገኝ እየተደረገ ያለው ጥረት አበረታች መሆኑን ተናግረዋል።
ለዚህ መሳካት የሚኒስቴሩ ድጋፍ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል።
ሚኒስቴሩ ቀደም ሲል በክልሉ የዓሳ ሀብት ልማቱን ለማዘመን የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ሶስት የዓሳ ማቀነባበሪያና የግብይት ማዕከላት ግንባታን ጨምሮ የዓሳ ማጥመጃና ማቆያ የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን ድጋፍ ማድረጉን አስታውሰዋል።
በቀጣይም የዘርፉን ልማት በማዘመን ሀብቱ ለክልሉ ብሎም ለሀገር የኢኮኖሚ ግንባታ እንዲውል እየተደረገ ላለው ጥረት ሚኒስቴሩ የጀመራቸውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን ከመደገፍ ባለፈም በዘርፉ ለተሰማሩ ወጣቶች የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸው ጭምር እገዛ እንደሚደረግም ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ በክልሉ ሰፊ የዓሳ ሀብት ቢኖርም በዘመናዊ መልኩ በማልማትና ጥቅም ላይ በማዋል ረገድ ውስንነቶች መኖራቸውን አንስተዋል።
የዓሳ ሀብቱን ዘመናዊ የገበያ ሰንሰለት በመጠቀም ወደ ገበያ የማቅረቡ ስራ እንዳለ ሆኖ በቋንጣ መልክ እየተዘጋጀ ለገበያ እየቀረበ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
በመሆኑም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተጀመሩት የቴክኖሎጂ ድጋፍና እገዛዎች እንዲጠናከሩ ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ ጠይቀዋል።
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እየተደረጉ ካሉት የቴክኖሎጂ ግብዓት ድጋፎች በተጨማሪ የቴክኒክ እገዛ ጭምር ያስፈልጋል ያሉት ደግሞ የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፖል ጋሪ ናቸው።
በጋምቤላ ክልል በዓመት እስከ 20 ሺህ ቶን ዓሳ ማምረት የሚያስችል አቅም እንዳለ ከክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሀብት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025