አዲስ አበባ፤ግንቦት 20/2017(ኢዜአ)፦የአፍሪካ ኢንሹራንስ ድርጅት ጉባኤ አህጉራዊ የመድኅን አገልግሎት የሚያስችሉ ልምዶች የተቀሰሙበት መሆኑን የድርጅቱ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የኢትዮጵያ መድኅን ሰጪዎች ፕሬዝዳንት አቶ ያሬድ ሞላ ገለጹ።
''የክፍያ ሚዛንን ማስተካከል፥ የአፍሪካ የእዳ ጫና፣ የሃገራት እዳ የኢንሹራንስ ድርጅቶች ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራል?" በሚል መሪ ሃሳብ የተካሄደው የአፍሪካ ኢንሹራንስ ድርጅት ዓመታዊ ጉባኤ ተጠናቋል።
የድርጅቱ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የኢትዮጵያ መድኅን ሰጪዎች ፕሬዝዳንት አቶ ያሬድ ሞላ፥ጉባኤው በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ምክክር በማድረግ መግባባት የተፈጠረበት መሆኑን ገልጸዋል።
ከአፍሪካና ከሌሎች የዓለም ክፍል 93 ሀገራትን የወከሉ ከ1 ሺህ 900 በላይ ተሳታፊዎች በጉባኤው መገኘታቸውን ገልጸው፥ ይህም በድርጅቱ የጉባኤ ታሪክ ከፍተኛው ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ ጉባኤውን በስኬት ማስተናገዷ ተሳታፊ ልዑካን ቡድኖችን ያስደመመ ክስተትና ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ምስጋና የቀረበበት መሆኑን ተናግረዋል።
የሀገራትን የዕዳ ጫና በሚመለከት የቀረቡ ጥናታዊ ጽሁፎች ለሕግ አውጪዎችና ኢንሹራንስ አስተዳዳሪዎች በማሰራጨት ለፖሊሲ ግብዓትነት ማዋል የሚያስችል ምክክር መደረጉን ገልጸዋል።
ከመድኅን አገልግሎት ዕድገት፣ስርጸትና የነፍስ ወከፍ መጠን መለኪያ አንፃር ብዙ ስራዎች ይጠብቁናል ነው ያሉት።
በጉባኤውም ኢትዮጵያን ጨምሮ የአፍሪካን የመድኅን አገልግሎት ለማሳደግ የሚያስችሉ ልምድና ተሞክሮዎች ጠንካራ የመድህን ስርዓትና አገልግሎት ከገነቡ ሀገራት መቀሰማቸውን አንስተዋል።
የአፍሪካ መድኅን ድርጅት ፕሬዝዳንት ፓቲ ማርቲን፥የጋራ ትብብርን በማጠናከር የአፍሪካን መድኅን ኢንዱስትሪ ለማሳደግ ገንቢ ምክክር ተደርጓል ብለዋል።
የኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ጉባኤው በስኬት እንዲጠናቀቅ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ ጠለፋ መድኅን አክሲዮን ማኅበር ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚና የመድኅን ባለሙያዎች ማኅበር ምክትል ፕሬዝዳንት ፍቅሩ ጸጋዬ፥በኢትዮጵያ ሀገር በቀል የመረዳጃ ማህበራትን ጨምሮ እድሜ ጠገብና ዘመናዊ የመድኅን ሰጪ ተቋማት መኖራቸውን ገልጸዋል።
በመላ ሀገሪቱ የህይወት፣ ንብረትና የሕጋዊ ኃላፊነት መድኅን አገልግሎት የሚሰጡ 18 የመድኅን አገልግሎት ሰጪ ኩባንያዎች እንዳሉ ተናግረዋል።
በጉባኤው የቀረቡ የመነሻ ጽሁፍ ምክረ ሃሳቦችን ለኢትዮጵያ መድኅን አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዕድገት ጥቅም ላይ እንዲውሉ ይደረጋል ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025