
አዲስ አበባ፤ግንቦት 21/2017(ኢዜአ)፦የቱሪዝም ሚኒስቴር መስፈርቱን ላሟሉ 11 ሆቴሎች ባለ አምስት ኮከብ ደረጃ መስጠቱን አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ በ2017 በጀት ዓመት በአዲስ አበባ የሚገኙ ነባር እና አዳዲስ ሆቴሎችን ዳግሞ ምዝና በማድረግ አስገዳጅ መስፈርቶችን ላሟሉ ሆቴሎች የኮከብ ደረጃ መስጠቱን ይፋ አድርጓል።
በሚኒስቴሩ የቱሪስት አገልግሎቶች ብቃት ማረጋገጥና ደረጃ ምደባ መሪ ስራ አስፈጻሚ ታሪኩ ደምሴ፥ ደረጃ ከተሰጣቸው ሆቴሎች ውስጥ 34ቱ በዳግም ምዘና ስድስቱ ደግሞ አዲስ አገልግሎት የጀመሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የምዘና መስፈርቶች የሆቴል ውጫዊ ገጽታ፣ማብሰያ፣የሆቴሉ ጠቅላላ አገልግሎት፣ጥበቃና ደህንነትን ጨምሮ 12 ዋና ዋና ነጥቦችን ያካተተ ነው ብለዋል።
ስካይላይትና ሸራተን አዲስ ሆቴልን ጨምሮ 11 ሆቴሎች ባለ 5 ኮከብ ደረጃ፣ 9 ሆቴሎች ባለ 4 ኮከብ እንዲሁም 7 ሆቴሎች ባለ 3 ኮከብ፣ አምስት ሆቴሎች ባለ2 እንዲሁም ሁለት ሆቴሎች ባለ አንድ ኮከብ ደረጃ ማግኘታቸውን ተናግረዋል።
አዲስ የተመዘኑ ስድስት ሆቴሎች ከባለ አራት እስከ ባለ ሁለት ኮከብ ደረጃ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል።
የተሰጠው ደረጃ በአዲስ አበባ እያደገ የመጣውን የኮንፈረንስ ቱሪዝም የሚመጥን አገልግሎት በመስጠት ከቱሪዝም ዘርፍ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ ጉልህ ድርሻ አለው ተብሏል።
በሆቴሎች መካከል ጤናማ ውድድር እንዲኖርና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግም ያግዛል ብለዋል።
የኮከብ ደረጃው ለ3 ዓመት የሚያገለግል ሲሆን በሚደረገው ክትትልና ቁጥጥር ከደረጃ በታች የወረደ ሆቴል በማንኛውም ጊዜ ደረጃውን ሊነጠቅ እንደሚችል አስገንዝበዋል።
በኢትዮጵያ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማልማት ዘርፉ ለምጣኔ ሃብት እድገት ያለውን ድርሻ ለማሳደግ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026