ነቀምቴ ፤ ግንቦት 21/2017 (ኢዜአ)፤-በመኽር ወቅቱ በቆሎን በኩታ ገጠም በማልማት ለገበያ ለማቅረብ እየሰሩ መሆናቸውን በምስራቅ ወለጋ ዞን የጉቶ ጊዳ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለጹ።
በምሰራቅ ወለጋ ዞን በዘንድሮ መኽር ወቅት 80ሺህ 820 ሄክታር ኩታገጠም ማሳ ላይ በቆሎ እንደሚለማ የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታውቋል ።
በዞኑ በመኽር ወቅቱ ቀድመው ከሚዘሩ ሰብሎች አንዱ በቆሎ ሲሆን በዞኑ የጉቶ ጊዳ ወረዳ የኩታ ገጠም በቆሎ ልማት የዘር ስራ ዛሬ ተጀምሯል።
የወረዳው ነዋሪ አርሶ አደር አስፍው ለማ እንደተናገሩት የአካባቢው አርሶ አደሮች 1ሺ 33 ሄክታር መሬት ላይ በቆሎን በኩታገጠም በማልማት ለገበያ ለማቅረብ ዘር መዝራት ጀምረዋል ።
በቆሎን በተሻለ ጥራትና ብዛት በስፋት ለማልማት አቅደው ወደ ስራ መግባታቸውን ጠቁመው በግብርና ፅህፈት ቤት በኩል አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል።
ሌላው የወረዳው ነዋሪ አርሶ አደር ወርቅነህ ገለታ በበኩላቸው ሰብልን በተናጠል ማልማት ውጤቱ እንብዛም መሆኑን ጠቁመው በኩታገጠም ማልማት አቅምን በማጎልበት የተሻለ ምርት እንደሚያስገኝ ተናግረዋል ።
አርሶ አደሮች በኩታ ገጠም በመደራጀት አንድ ሺ ሄክታር መሬት ላይ በቆሎ በማልማት ከ80ሺ ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት አቅደው የዘር ስራ መጀመራቸውን አመልክተዋል ።
የምስራቅ ወለጋ ዞን ግብርና ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አስፍው ሀንቢሳ በዞኑ በዘንድሮ መኽር ወቅት ከ80ሺ 820 ሄክታር በላይ መሬት በኩታ ገጠም በበቆሎ ዘር የመሸፈን ስራ መጀመሩን ተናግረዋል።
ለልማቱ የሚያገለግል 22ሺ ኩንታል የበቆሎ ምርጥ ዘር ቀርቦ እስካሁን ከ19ሺ ኩንታል በላዩ መከፍፈሉን ተናግረዋል ።
የማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጭትም እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል ።
የሰብሉን ምርታማነት ለማሳደግ የእርሻ ስራውን የማዘመንና ለኩታገጠም አስተራረስ ዘዴ ትኩረት መሰጠቱን አስታውቀዋል ።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025