
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 26/2017(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አራተኛውን እና የክረምት በጎ ፍቃድ ስራ አካል የሆነውን የገጠር ኮሪደር ልማት ስራ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን ሁልባረግ ወረዳ ወራበት ሻማ ቀበሌ ሞዴል የአርሶ አደሮች የመኖሪያ መንደር ግንባታ አስጀምረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት አራተኛውን እና የክረምት በጎ ፍቃድ ስራ አካል የሆነውን የገጠር ኮሪደር ልማት ስራ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን ሁልባረግ ወረዳ ወራበት ሻማ ቀበሌ ሞዴል የአርሶ አደሮች የመኖሪያ መንደር ግንባታ አስጀምረናል ብለዋል።
እነዚህ መኖሪያዎች ተገንብተው ሲጠናቀቁ የአርሶ አደሩን የኑሮ ዘዬ የሚቀይሩ እና ጤናማ ህይወትን የሚያላብሱት ናቸው ሲሉም ገልጸዋል።

በሌላ በኩል በዞኑ በነበረን ቆይታ የግሉ ዘርፍ በአግሮ ኢንደስትሪ ላይ ያለውን ተሳትፎ ተመልክተናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።
እንደማሳያ አቶት የተቀናጀ አግሮ ኢንደስትሪን ተዘዋውረን ተመልክተናል ነው ያሉት።
እንዲህ ያሉት ስራዎች በሌማት ትሩፋት ውጤት ለማስመዝገብ የተጀመረውን ተግባር ከግብ ለማድረስ በጎ ጅምሮች በመሆናቸው ሊበረታቱ ይገባል ብለዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026