
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 27/2017(ኢዜአ)፦ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተያዘውን ራዕይ እውን ለማድረግ በተከናወኑ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶ/ር) ገለጹ።
የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን በጥራት መንደር ውስጥ የተረከበውን ህንጻ ምርቃት መርሃ ግብር አካሂዷል።

በመድረኩ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶ/ር)፣ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ጌታቸው እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተያዘውን ራዕይ እውን ለማድረግ በተከናወኑ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት እየተመዘገበ ነው።

የጥራት መንደሩ ለኢኮኖሚ ዕድገት ጉልህ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑን አንስተው፤ መንደሩ ለኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ የሆኑ ተቋማት በቅንጅት የሚሰሩበት መሆኑን ጠቁመዋል።
ይህም ኢትዮጵያን በአፍሪካ በጉልህ የሚያስቀምጣት መሰረተ ልማት መሆኑን ተናግረዋል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን በጥራት መንደር እንዲገቡ ከተፈለጉ ተቋማት መካከል አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።
የጥራት መንደር የኢትዮጵያን የልማት መሻት የዋጀ የነገ ፍላጎታችንም ማሳያ እንዲሁም ለትውልድ የሚተርፍ ጸጋ መሆኑን ገልጸዋል።
የባለስልጣኑ ሰራተኞች በግቢው ያሉ መሰረተ ልማቶች እንዲጠበቁ የራሳቸውን ሚና እንዲወጡም አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ጌታቸው የተረከቡት ህንጻ ባለስልጣኑ የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ መወጣት የሚያስችለው መሆኑን ተናግረዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026