
አርባ ምንጭ፤ ግንቦት 27/2017(ኢዜአ)፦ አመራሩ በለውጥ እሳቤ ታግዞ ለውጥ ፈጣሪ ማህበረሰብ የመፍጠር ሃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት እንዳለበት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል አስታወቁ።
በአርባ ምንጭ ከተማ ለሦስት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የፐብሊክ ኢንተርፕሪነርሽፕና ኢኖቬሽን ስነ-ምህዳር ግንባታ የአመራሮች ስልጠና ተጠናቋል።

በማጠቃለያ መድረኩ የተገኙት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ባስተላለፉት መልዕክት አመራሩ በለውጥ እሳቤ ታግዞ ለውጥ ፈጣሪ ማህበረሰብ የመፍጠር ሃላፊነቱን በአግባቡ ሊወጣ ይገባል ብለዋል።
የበለጸገ ክልልና ሀገር እንዲፈጠር በየደረጃው ያለው አመራር ጊዜውን የዋጀ የዕውቀትና ክህሎት ትጥቅ በመታጠቅ ለህብረተሰቡ ፈጠራ የታከለበት የሥራ ምህዳር መፍጠር ይኖርበታል ሲሉም አክለዋል።
በማያቋርጥ የለውጥ ሂደት ውስጥ ነን ያሉት ሚኒስትሯ፣ አመራሩ በየአካባቢው ያሉ ፀጋዎች ለህዝብ ጥቅም እንዲውሉ በማድረግ ታሪካዊ ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበትም አስገንዝበዋል።
የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ከመንግስት ሀብት የሚፈልጉ ሳይሆን የራሳቸውን ሀብት የሚፈጥሩ መሆን እንዳለባቸው ጠቁመው፣ በየአካባቢው ያሉ ፀጋዎችን ጥቅም ላይ ለማዋል በሚሰራው ሥራ በቴክኖሎጂ ሽግግር የበኩላቸውን መወጣት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
በለውጥ እሳቤ መሰረት የሥራ ዕድልን ከፈጠራ ጋር በማስተሳሰር ውጤታማ ሥራዎችን ለማከናወን ከአመራሩ ብዙ ይጠበቃል ሲሉም ተናግረዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በበኩላቸው የአመራር ስልጠና በሀገር ደረጃ የተጀመረውን የለውጥ እሳቤ በአግባቡ በመረዳት ለችግሮች ሀገር በቀል መፍትሄ መስጠት እንደሚያስችል ገልጸዋል።
ባለፉት ሰባት ዓመታት በሀገር ደረጃ የነበሩ ስብራቶችን ለመጠገን ሥራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ገልጸው፣ በዚህም ፈተናን ወደ ዕድል ዕዳን ወደ ምንዳ መቀየር ተችሏል ብለዋል።
በክልሉ ልማትን በማጠናከር ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ጸጋዎች እንዳሉ ጠቁመው፣ አመራሩ በስልጠና ባገኘው እውቀት ታግዞ ጸጋዎችን በማልማት ለሥራ አጥነት ችግር መፍትሄ መስጠት እንዳለበት አሳስበዋል።
ስልጠናውን ያልወሰዱ ቀሪ አመራሮችን በማሰልጠን የለውጡ እሳቤ ወጥነት ባለው መንገድ እንዲሳካ የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

የሥራ አጥነት ችግርን በቅጥር ብቻ ማስወገድ አይቻለም ያሉት የፌደራል ኢንተርፕሪነርሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሀሰን ሁሴን(ዶ/ር) ለዜጎች ምቹ የፈጠራ ምህዳር መፍጠር ያስፈልጋል ነው ያሉት።
ለወቅቱ ችግሮች ወቅቱን የሚመጥን መፍትሄ በመስጠት አመራሩ ስልጠናውን በተግባር ማሳየት እንዳለበትም ተናግረዋል።
በስልጠናው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እና በሥሩ የሚገኙ የ12 ዞኖች ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026