አዲስ አበባ፤ ግንቦት 27/2017(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ በ2022 የፌደራል መንግስት ገቢ 3 ነጥብ 5 ትሪሊዮን ብር ለማድረስ የተያዘውን ግብ ለማሳካት ግብርን በፈቃደኝነት መክፈል ባህል ሊሆን እንደሚገባ የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ ገለጹ፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና ገቢዎች ሚኒስቴር "ለሁለንተናዊ ብልፅግና የንግዱ ማህበረሰብ ሚና" በሚል መሪ ሀሳብ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ምክክር አድርገዋል፡፡
የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፤ መንግስት የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በማድረግ የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ማሳደግ፣ ምርትና ምርታማነትን መጨመር፣ የስራ ዕድል ፈጠራን ማሳደግተችሏል፡፡
ይሄውም ኢትዮጵያ ከዓለም የኢኮኖሚ ስርዓት በተቃራኒ ስትጓዝበት የነበረውን አካሄድ በማስቀረት ፍትሐዊ የንግድ ውድድር እንዲፈጠር አስችሏል ብለዋል፡፡
የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ትግበራን እና የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነትን በፍጥነት በማጠናቀቅ የሀገር ውሰጥ ምርትና አገልግሎት እንዲሳለጥ ይደረጋል ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ግብርን በፈቃደኝነት መክፈል ባህል አልሆነም ያሉት ሚኒስትሯ፤ በ2022 የፌደራል መንግስትን ገቢ 3 ነጥብ 5 ትሪሊዮን ብር ለማድረስ የተያዘውን ግብ ለማሳካት በቂ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
በ2011 በጀት ዓመት የፌደራል መንግስት ገቢ 198 ቢሊዮን ብር ብቻ እንደነበር አስታውሰው፤ በ2017 በጀት ዓመት አስር ወራት 743 ነጠብ 8 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን ጠቁመዋል፡፡
በመሆኑም የግሉ ዘረፍ መንግስት የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ተጠቅሞ የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ መደገፍ ይገባዋል ብለዋል፡፡
አስተያየት የሰጡ የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው፤ መንግስት የግሉን ዘርፍ ለማበረታታትና የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ የተግባር እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በአንድ ማዕከል አገልግሎት እንዲሁም የንግድ ምዝገባና ፈቃድ በኦንላይን በመስጠት ከሌብነት የፀዳና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ማስቻሉንም ተናግረዋል፡፡
ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የጥራት መንደር በመገንባት ለዓለም ገበያ የምናቀርበው ምርት ጥራት ያለውና ተወዳዳሪ እንዲሆን ያግዘናልም ብለዋል፡፡
በተጨማሪም መንግስት የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ትግበራን በማቀላጠፍና በኮሜሳ የምንሳተፍበትን ዕድል በማመቻቸት ለውጭ ገበያ ያዘጋጀነውን ምርት እንድናቀርብ ምቹ ሁኔታ ሊፈጥርልን ይገባል ሲሉም ጠይቀዋል፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) በሰጡት ማጠቃለያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ትግበራ በተያዘው ወር እንደሚጀመር ገልጸዋል፡፡
መንግሥት የ90 በመቶ የወጪ ገቢ ንግድ ታሪፍን ነጻ የሚያደርግ አሰራር ማሻሻያ በማድረግ ትግበራውን ወደ ማይቀለበስ ደረጃ አድርሶታል ብለዋል፡፡
በመሆኑም አምራቶች በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ተወዳዳሪ መሆን የሚያስችላቸውን ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025