አዲስ አበባ፤ ግንቦት 30/2017(ኢዜአ):- ኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ጥያቄዋ በንግግርና በህግ አግባብ መልስ እንዲያገኝ የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ ኢትዮጵያ ወደብ ያጣችበት መንገድ በጣም ያስቆጨኛል ሲሉ ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገሪቷ ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ወደብ እንደሌላት ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት መሆን አለባት የሚለው ጉዳይ ዘመን አመጣሽ አጀንዳ አለመሆኑን መገንዘብ እንደሚገባም አመልክተዋል።
ማንንም ሳንጎዳ የኛን ጉዳት መቀነስ እንዳለብን አምናለሁ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ወደብ አልባ በመሆኗ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባት ተናግረዋል።
በዓለም በወደብ አልባ ሀገራት ልምምድ የሌለ ግፍ በኢትዮጵያ ላይ መፈጸሙንና ይህ ጉዳይ አፋጣኝ መፍትሄ ሊያገኝ እንደሚገባ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ ላይ ኢትዮጵያ ሰላማዊ በሆነ መንገድ በቀይ ባህር ላይ የባህር በር ያስፈልጋታል ሲሉ መግለጻቸው አይዘነጋም።
በማብራሪያቸውም፥ የባህር በር ጥያቄን በተመለከተ በሰጡት ገለጻ ኢትዮጵያ በባህር በር ጉዳይ ላይ ወደ ኋላ የማይል ይፋዊ አቋም እንዳላት ተናግረዋል።
ነገር ግን ይህን ለማሳካት ጦርነትም ሆነ የኃይል አማራጭ አንፈልግም ፍላጎታችንን ማሳካት የምንሻው በሰላማዊ መንገድ ነው ብለውም ነበር።
የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ምክንያታዊና ፍትሃዊ ጥያቄ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እኛ ባናሳካው ልጆቻችን ያሳኩታል ሲሉ መናገራቸው የሚታወስ ነው።
#Ethiopian_News_Agency
#ኢዜአ #Ethiopia
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025