ሰኔ 1/2017(ኢዜአ)፦ በክልሉ በመኸር እርሻ ከ8 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በኩታ ገጠም እየለማ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ሀላፊ በሪሶ ፈይሳ፤ በምርት ዘመኑ ሰፊ መሬትና የሰው ሃይልን በማቀናጀት በቴክኖሎጂ የታገዘ የግብርና ልማት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
በተያዘው መኸር 10 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በማልማት 368 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ማግኘት የሚያስችል የተቀናጀ የልማት ስራ እየተከናወነ መሆኑንም ተናግረዋል።
በእስካሁኑ ሂደትም 2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች መሸፈኑን ነው አቶ በሪሶ የገለጹት።
በመኸር እርሻ ከ8 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በኩታ ገጠም እየለማ መሆኑን ጠቅሰው ለምርት ዘመኑ የአፈር ማዳበሪያና የምርጥ ዘር ስርጭት እየተከናወነ ይገኛልም ብለዋል።
ከ5 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት አሁን ላይ በትራክተር እየለማ መሆኑንም ተናግረዋል።
በአንዳንድ አካባቢዎች ለደረሱ ሰብሎች የጥበቃና እንክብካቤ ከማድረግ በተጨማሪ የምርት አሰባሰብ ሂደቱ ብክነትን የሚቀንስ እንዲሆን እገዛና ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
በክልሉ አምራቹንና ሸማቹን ተጠቃሚ ማድረግ የሚያስችል የገበያ ጥናት በማካሄድ ከባለሀብቱ ጋር የማገናኘት ስራ እየተከናወነ ይገኛልም ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025