አዲስ አበባ፤ ሰኔ 3/2017(ኢዜአ)፦ በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ የኢትዮጵያ እምቅ የኢንቨስትመንት አቅምን ጥቅም ላይ ለማዋል ዘመኑን የዋጀ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ላይ ይበልጥ በማተኮር እንደሚሰራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ ገለጹ።
የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የመሪዎችና ባለሙያዎች ስብሰባ "አዳዲስ መዳረሻዎችን ማሰስ፣ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አንቀሳቃሽ" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ነው።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ እንዳሉት፤ መድረኩ ለውጭ ጉዳይ ስራዎች መሰረት የሆነውን የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ለማጠናከር ያግዛል።
የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ በሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች የተፈጠሩ ምቹ የኢንቨስትመንት እድሎችን ከሀገር ውስጥ ባለፈ የውጭ ኢንቨስተሮች እንዲጠቀሙባቸው የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ አቅሞች ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር በንግድ ኢንቨስትመንትና በሌሎች ዘርፎች ለማስተሳሰር ጠንካራ ዲፕሎማሲ ለመፍጠር ይሰራል ብለዋል።
ለዚህ ደግሞ የኢትዮጵያ ዕምቅ አቅም ለውጭ ባለሀብቶችና ኢንቨስተሮች በሚገባ ማስተዋወቅ የሚያስችል ዘመኑን የዋጀ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ እንደሚደረግም ተናግረዋል።
ለሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያው ስኬታማነት የውጭ ባለሀብቶችና ኩባንያዎች ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን በመግለፅ፣ በዚህም በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የተፈጠሩ ዕድሎችን በሚገባ ለማሳወቅ ይሰራል ነው ያሉት።
የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ የመንግሥት ብቻ ሳይሆን የሁሉንም ተሳትፎ ይጠይቃል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማሻገር በቅንጅት እንደሚሰራ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን(ዶ/ር) ኢትዮጵያ በጸጋዋ ልክ እንድትለማ አቅሟን በማስተዋወቅ ጠንካራ የኢኮኖሚ አጋሮችን መፍጠር ይገባል ብለዋል።
ኮሚሽኑ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት አማራጮችን በሚገባ ለማስተዋወቅ "የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ስትራቴጂ" ተግባራዊ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑንም ገልጸዋል።
አየርላንድ፣ እስራኤል እና ሌሎች የካሪቢያን ሀገሮች የኢንቨስትመንት አቅማቸውን ማሳደግ የቻሉት የተሻሉ ኢንቨስተሮች በመመልመል መሆኑን ገልጸው፣ ኢትዮጵያም በዚህ ላይ ትኩረት ታደርጋለች ብለዋል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ተወዳዳሪና ተመራጭ የውጭ ኢንቨስትመንት መዳረሻ መሆኗን ጠቅሰው፣ ካላት እምቅ አቅም አንፃር ብዙ መስራት ይጠበቅብናል ነው ያሉት።
የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት እና ዲፕሎማሲ ቢዝነስ ተኮር ማድረግ የሚያስችል ተሻጋሪ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ዘላቂ ማድረግ የሚያስችል የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መደረጉን ጠቅሰው፣ ለስኬታማነቱ ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በትብብር መስራት ይገባል ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025