
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 4/2017(ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል በክረምቱ ወቅት የፍራፍሬ ችግኝ በ5 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ በኩታ ገጠም እንደሚለማ የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የቡናና ሻይ ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሀመድ ሳኒ አሚን እንዳሉት በዘንድሮ የክረምት ወቅት በተለይ በዓለም ገበያ ተፈላጊ የሆኑ ተክሎችን ለማልማት ሰፊ ዝግጅት ተደርጓል።
ለዚህም የተለያየ ጠቀሜታ ያላቸው የፍራፍሬ ምርጥ ዘር በማባዛት በልዩ ሁኔታ በኩታ ገጠም ለማልማት በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

በአጠቃላይ በክረምቱ 200 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የፍራፍሬ ችግኝ ለማልማት መታቀዱን ገልጸው ከዚህ ውስጥ 5 ሺህ ሄክታሩ በኩታ ገጠም የሚለማ መሆኑን ገልጸዋል።
በአጠቃላይ ከሚለማው መሬት 500 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት መታቀዱን ገልጸው ልማቱም በሰባት ዞኖች ውስጥ በሰፊው እንደሚከናወን ተናግረዋል።
በክረምቱ ወራት የሚተከሉት 12 ዓይነት የፍራፍሬ ችግኞች ሲሆኑ እስካሁንም 450 ሚሊዮን የፍራፍሬ ችግኞች መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል።
ችግኞቹም በዋናነት አቮካዶ፣ ሙዝ፣ ፓፓያ፣ አፕልና ብርቱካንን የሚያካትት ሲሆን ልማቱም በጅማ፣ በቡኖ በደሌ፣ በኢሉአባቦር፣ በ አራቱም የወለጋ ዞኖች፣ በጉጂ፣ በቦረና፣ በአርሲና በባሌ እንደሚከናወንም ለማሳያነት ጠቅሰዋል።

በአሁኑ ጊዜ የመሬት መረጣና ዝግጅት መደረጉን ገልጸው በአንዳንድ አካባቢዎች ተከላ መጀመሩንም ተናግረዋል።
በክልሉ የፍራፍሬ ልማት በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱን ገልጸው ባለፉት ሶስት ዓመታት የተተከሉ ፍራፍሬዎች አሁን ላይ በሀገር ውስጥና በዓለም ገበያ ላይ በማቅረብ የውጭ ምንዛሪ ማስገኘት መጀመሩን ተናግረዋል።
በልማቱ ላይ የሚሳተፉ አርሶ አደሮች በቴክኖሎጂና በአቅርቦት አያያዝ ላይ ስልጠና የሚሰጥ መሆኑን ጠቅሰው የማይቋረጥ የባለሙያ ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግላቸውም አስረድተዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026