
ሆሳዕና፤ ሰኔ 5/2017(ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳምንቱን ሙሉ አገልግሎት የሚሰጡ የግብይት ማዕከላትን በማጠናከር የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመረው ተግባር እንደሚጠናከር የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) ገለፁ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ ሳምንቱን ሙሉ ግብይት የሚፈጸምባቸው የገበያ ማዕከል ግንባታን ዛሬ በሆሳዕና ከተማ አስጀምረዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንዳሉት በሀገር አቀፍ ደረጃ የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት የቅዳሜና እሁድ ገበያን ለማጠናከር ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል፡፡

በዚህም በሳምንት ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚከናወነውን ገበያ ሳምንቱን ሙሉ እንዲከናወን በማድረግ አምራቹንና ሸማቹን የማገናኘት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
አርሶ አደሩ ምርቱን በየዕለቱ እንዲያቀርብ በማድረግ የዋጋ ንረትን ለመከላከል እየተሰራ ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡
በክልሉ ሳምንቱን ሙሉ የግብይት አገልግሎት የሚሰጡ የገበያ ማዕከላትን በማጠናከር የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመረው ተግባር እንደሚጠናከርም አረጋግጠዋል፡፡

የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዳንኤል ዳምጠው፤ በክልሉ አምራቹንና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት የዋጋ ንረትን መከላከል የሚያስችሉ 100 የቅዳሜና እሁድ እንዲሁም 43 ሳምንቱን ሙሉ ግብይት የሚከናወንባቸው ማዕከላት ተቋቁመው አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡
ሳምንቱን ሙሉ ግብይት የሚከናወንባቸው ማዕከላትን ማጠናከር በማህበረሰቡ ላይ የሚደርስን የኑሮ ውድነት ጫና ለመከላከል የክልሉ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡

የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ማቲዎስ አኒዮ በበኩላቸው ሳምንቱን ሙሉ ግብይት የሚከናወንባቸው ማዕከላትን በማጠናከር አምራቹንና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት የኑሮ ውድነትን መከላከል ያስችላል ብለዋል፡፡
በከተማው የተጀመረው የግብይት ማዕከል ግንባታ ለማህበረሰቡ አስፈላጊ የሆኑ የዕለት ተዕለት ፍጆታዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ የማግኘት ዕድል ይፈጥራል ሲሉም አክለዋል።
በመርሐ ግብሩ የክልሉ መንግሥት ዋና ተጠሪ ዲላሞ ኦቶሬ(ዶ/ር) እንዲሁም የክልሉ፣ የሀዲያ ዞንና የሆሳዕና ከተማ አመራር አባላትና ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ሰኔ 2 /2018 (ኢዜአ)፦የዕቃ ማከማቻ ደረሰኝ ሥርዓት ደንብ የግብርና ኢኮኖሚ ሽግግርን በማሳለጥና የገጠር ልማትን በማጎልበት አርሶ አደሮችን ተጠ...
Jun 10, 2026
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 1/2018 (ኢዜአ)፦ በመዲናዋ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን በማላቅ የተገልጋዮችን እርካታ የሚያሳድጉ ሰው ተኮር ተግባራት ተጠናክረው እንደ...
Jun 9, 2026
ሀዋሳ ፤ ግንቦት 28/2018 (ኢዜአ) ፦በይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ማቀነባበሪያ ፓርክ ከአምራች ኢንዲስትሪዎች ጋር በተፈጠረላቸው የገበያ ትስስር ...
Jun 6, 2026
ነገሌ ቦረና፤ ግንቦት 19/2018(ኢዜአ)፦ የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት መጀመር የአካባቢውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የበለጠ የሚያ...
May 28, 2026