የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ኢትዮጵያ የተሻለ የግምገማ ስርዓት አላት -የአፍሪካ የግምገማ ማህበር

Jun 13, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 5/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ፖሊሲ በመቅረጽና በውሳኔ አሰጣጥ የተሻለ የግምገማ ስርዓት ካላቸው የአፍሪካ አገራት አንዷ መሆኗን የአፍሪካ የግምገማ ማህበር ገለጸ።

የአፍሪካ የግምገማ ማህበር ከፕላንና ልማት ሚኒስቴርና ሌሎች ተቋማት ጋር በመተባበር ከሰኔ 9 እስከ 11/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚያከብረውን 25ኛ አመት የምስረታ በዓል አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

ማህበሩ የአፍሪካ አገራት የሚተገብሯቸው ፖሊሲዎችና እቅዶች በጥናትና መረጃ ላይ የተመሰረቱ እንዲሆኑ ጠንካራ የግምገማ ስርዓት ለመዘርጋት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናና ምክረ ሃሳብ በመስጠት የሚሰራ ነው።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ጥሩማር አባተ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ጠንካራ የግምገማና ክትትል ስርዓት በመዘርጋት በመረጃና ጥናት ላይ የተመሰረተ የፖሊሲ ውሳኔዎችን ለመስጠት በርካታ ተግባራትን አከናውናለች።

ለግምገማ ስርዓት መሰረት የሆኑትን ተቋማዊ አቅም ማጠናከርና የሰው ሃይል ማብቃት እዲሁም በፖሊሰ ደረጃ ትኩረት እንዲሰጠው በማድረግ አሰራሮችን መዘርጋቷን ገልጸዋል።

በዚህም በጤና፣ ግብርና እና ሌሎች ዘርፎች የክትትልና ግምገማ ክፍሎችን በማቋቋም ከታች ጀምሮ መረጃዎችን በመሰብሰብ ለእቅድና ፖሊሲ ግብዓት እየዋሉ ይገኛሉ ብለዋል።

በሰው ሃይል ልማት ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ በመረጃ ላይ የተመሰረተ የምጣኔ ሃብት መርሃ ግብሮች ተቀርጸው ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ የግምገማ ስርዓቷን የበለጠ ጠንካራ ለማድረግ ከብሔራዊና አህጉራዊ ማህበራትና ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራች እንደምትገኝ ተናግረዋል።

የአፍሪካ የግምገማ ማህበር ፕሬዝዳንት ሚቼ ኦውድራጎ አፍሪካ ራሷ የግምገማ ስርዓትና እውቀት እንድትመራ እንደየአገራቱ ነባራዊ ሁኔታ ድጋፎችን በማድረግ ማህበሩ ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።

ማህበሩ ባለፉት 25 አመታት በመረጃ ላይ የተመሰረተ ፖሊሲና ውሳኔ አሰጣጥ እንዲጎለብት በአህጉራዊ እንዲሁም በብሔራዊ ደረጃ የግምገማ ስርዓትን በማጠናከር ከአገራት ጋር በትብብር ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰዋል።

በአህጉሪቱ የአገራት የግምገማ ስርዓት ጥንካሬ የተለያየ እንደሆነ ጠቅሰው ኢትዮጵያ የተሻለ የግምገማ ስርዓት ካላቸው አገሮች ውስጥ እንደሆነችም ገልጸዋል።

በማህበሩ 25ኛ አመት የምስረታ በዓል ላይ ለመሳተፍ የሚመጡ የአገራት ተወካዮችና ሙያተኞች ከኢትዮጵያ ታሪክና በራስ አቅም መልማት ተሞክሮ መቅሰም የሚችሉበት ይሆናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ የግምገማ ማህበር ፕሬዝዳንት ደረጄ ማሞ በበኩላቸው በአዲስ አበባ የሚካሄደው የአፍሪካ የግምገማ ማህበር የምስረታ በዓል በርካታ ቁጥር ያላቸው ተሳተፊዎች የሚገኙበትና ማህበሩ ያሳካቸውን ውጤቶች የሚገመገሙበት ትልቅ ሁነት መሆኑን ነው የገለጹት።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ ነው</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...

Feb 28, 2025

<p>በዞኑ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ ነው</p>

ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...

Feb 24, 2025

<p>የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተደረገ ነው - ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል</p>

አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...

Feb 24, 2025

<p>ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች ነው -የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...

Feb 12, 2025