
አዳማ፤ ሰኔ 7/2017(ኢዜአ)፦ የበረሃ አንበጣና ፀረ ተባይ መከላከያ ቴክኖሎጂን በስፋት በመጠቀም ምርታማነትን ለማሳደግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን ገለፀ።
ኮርፖሬሽኑ ከናሽናል ኤርዌይስና ከሌሎች ባለድርሻዎች ጋር በመሆን በቀጣይ የርጭት አውሮፕላን አገልግሎት ተደራሽነትን ማስፋትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችለውን ውይይት በአዳማ ከተማ አካሂዷል።

የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ፈለቀ ገዛኸኝ በወቅቱ እንደገለፁት የበረሃ አንበጣን ከመከላከል ባለፈ የሰብል ምርትና ምርታማነትን የሚቀንሱ ተባዮች ለማጥፋት ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ጥቅም ላይ እንዲውሉ እየተደረገ ነው።
ኮርፖሬሽኑ የራሱ በሆነ 10ሺህ ሄክታር መሬት ላይ በ22 የሰብል ዓይነቶች ምርጥ ዘር እያባዛ መሆኑን ተናግረዋል።
ኮርፖሬሽኑ አሁን ላይ ተጨማሪ 5ሺህ ሄክታር መሬት ወደ እርሻ በማስገባት የተለያዩ የሰብል ምርጥ ዘሮችን በጥራትና በብዛት ለማምረት ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።
ከናሽናል ኤርዌይስ ጋር በመተባበር በ6ሺህ ሄክታር ላይ የለሙ የተለያዩ የምርጥ ዘር ሰብሎች በአረም፤ በተባይና በሌሎች ተያያዥ የሰብል በሽታዎች እንዳይጎዱ በአውሮፕላን ርጭት መካሄዱን ለአብነት ጠቅሰዋል።

የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ምክትል ስራ አስኪያጅ ጫላ አበበ በበኩላቸው ኢንተርፕራይዙ ከ32ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ ከ60 በላይ የሰብል ዝርያዎችን በማልማት የምርጥ ዘር ፍላጎትን ለማሟላት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ኢንተርፕራይዙ በ2016/17 ምርት ዘመን ከ800ሺህ ኩንታል በላይ የተለያዩ የሰብል ዓይነቶች ምርጥ ዘር ማምረቱን ጠቅሰው የፀረ አረምና ፀረ ሰብል በሽታ ማጥፊያ የርጭት አውሮፕላን በመጠቀሙና የሰብል እንክብካቤ ስራ በመስራቱ ከ160ሺህ ኩንታል በላይ ተጨማሪ ምርት ማግኘት መቻሉን አስታውቀዋል።
ድርጅቱ በዋናነት በምስራቅ ባሌና ባሌ፣ በአርሲና ምዕራብ አርሲ ዞኖች የስንዴ ልማት እንዲሁም በወለጋ በበቆሎ ምርጥ ዘር ላይ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
ኢንተርፕራይዙ በተለይ ከናሽናል ኤርዌይስ ጋር በመተባበር የምርጥ ዘር ብዜት ውጤታማነትን አሁን ካለበት ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።
በ2017/18 የምርት ዘመን ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለንን ቅንጅት በማጠናከር ምርታማነትን በተሻለ ደረጃ ለማሳደግ አቅደን እየሰራን ነው ሲሉም አክለዋል።

የናሽናል ኤርዌይስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ካፒቴን አበራ ለሚ በበኩላቸው ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የበረሃ አንበጣን ጨምሮ የአውሮፕላን ፀረ ተባይና ፀረ መድኃኒቶች ርጭት አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያን የግብርና ዘርፍ ዕድገት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን የማቅረብ ስራ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
በቀጣይም በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ከኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ጋር ተፈራርመዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026