የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ረቂቅ አዋጁ ሲጸድቅ የህዝብ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ነው

Jun 20, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ሰኔ 11/2017(ኢዜአ)፦የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ የማይንቀሳቀስ ንብረት ወይም ይዞታ ባለቤት እንዲሆኑ የሚፈቅደው ረቂቅ አዋጅ ጸድቆ ተግባራዊ ሲደረግ የህዝብ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ መሆኑን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሰረተ ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ።

ቋሚ ኮሚቴው የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት ወይም ባለይዞታ እንዲሆኑ በሚፈቅደው ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ የባለድርሻ አካላት የግብዓት ማሰባሰቢያ ውይይት አካሒዷል።

የውጭ ዜጎች የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለይዞታ መሆን የሚያስችል አዋጅን ለማሻሻል ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱ ይታወቃል።

በውይይቱ ላይ የረቂቅ አዋጁን ይዘትና አተገባበር በሚመለከት ገለጻ ቀርቧል።

የከተማ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ መሃመድ አብዶ (ፕ/ር) በውይይቱ ከባለድርሻ አካላት የተነሱ አስተያየቶች ረቂቅ አዋጁን ይበልጥ ለማጠናከር የሚያግዙ ናቸው ብለዋል።


በመሆኑም የተነሱ ሃሳቦችን በመለየት በረቂቅ አዋጁ ላይ እንዲካተቱ የማድረግ ስራ በትኩረት ሊከናወን እንደሚገባ አሳስበዋል።

ረቂቅ አዋጁ ጸድቆ ተግባራዊ ሲደረግ የህዝብ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ በመሆኑ ለተፈጻሚነቱ ጥረት ማድረግ ይገባል ነው ያሉት።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ረቂቅ አዋጁ ሊያሳካ የተፈለገውን ጉዳይ እውን ለማድረግ የጋራ ርብርብ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር) ፤ ረቂቅ አዋጁ ህጋዊነትን ለማረጋገጥና አሰራርን ለማበጀት የሚያግዝ በመሆኑ ወሳኝ ነው ብለዋል።


የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት አሸነፈች አበበ በበኩላቸው፤ ረቂቅ አዋጁ የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል አይነተኛ ሚና እንዳለው አብራርተዋል።

በረቂቅ አዋጁ የቤትና ሌሎች ግንባታዎችን በሚመለከት በተደነገገው ህግ የግልጸኝነትና የትርጓሜ ለውጥ እንዳያመጣ በድጋሚ የሚፈተሽበት አግባብ እንዲፈጠር ጠይቀዋል።


የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ተወካይ አቶ ጎሳ ደምሴ በበኩላቸው፤ በረቂቅ አዋጁ የሚካተቱ ህጎች ከባለድርሻ ተቋማት ጋር ተናባቢ ሆነው ሊዘጋጁ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ረቂቅ አዋጁ ከብሔራዊ ደህንነትና አገራዊ ጥቅም አኳያ ክትትልና ቁጥጥር የሚያደርግ ኮሚቴ የሚዋቀርበት እድል ቢያመቻች ለተአማኒነቱ አስቻይ ሁኔታን ይፈጥራልም ብለዋል።


የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካይ አቶ አስቻለው ከበደ ረቂቅ አዋጁ ኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ማዕከል ለማድረግ የሚከናወነውን ጥረት ያግዛል ብለዋል።

በዘርፉ ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ዲፕሎማት፣ የውጭ አገር ተቋማትና ዜጎች ተደጋጋሚ ጥያቄ ሲያቀርቡ መቆየታቸውን ጠቅሰው፤ ረቂቁ እነዚህ አካላት የሚስተናግዱበትን እድል ማመቻቸት እንደሚጠበቅበትም ገልጸዋል፡፡


የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ሔለን ደበበ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄና አሰተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም የውጪ አገር ዜጎች በኢትዮጵያ የሚያፈሩትን ሃብትና ንብረት በህግና በአሰራር በመደገፍ ፍትሃዊነትን ማረጋገጥ የረቂቅ አዋጁ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን አብራርተዋል።

በአሁኑ ወቅት የዜጎች ቀዳሚ ጥያቄ የቤት አቅርቦት መሆኑን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታዋ፤ መንግስት የቤት አቅርቦትን ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ስለመሆኑም ገልጸዋል።


በተለይም ከግሉ ዘርፍ ጋር በመቀናጀት በሚከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት ማምጣት የተቻለ ቢሆንም ካለው ፍላጎት አንጻር ግን አሁንም ውስንነቶች እንዳሉ ጠቁመዋል።

በመሆኑም ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን እድል በማስፋትና አሰራሮችን በማሻሻል የቤት ልማት ላይ የውጪ አገር ዜጎችና አልሚዎችን ማሳተፍ አስፈላጊ ሆኗል ብለዋል።

ይህም የቤት ልማት ዘርፉን በእጅጉ የሚያነቃቃ በመሆኑ ረቂቅ አዋጁ ላይ የተሰጡ አስተያየቶችን በትኩረት በማጤን አስፈላጊው የማሻሻያ ስራ እንደሚታከልበት አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ ነው</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...

Feb 28, 2025

<p>በዞኑ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ ነው</p>

ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...

Feb 24, 2025

<p>የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተደረገ ነው - ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል</p>

አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...

Feb 24, 2025

<p>ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች ነው -የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...

Feb 12, 2025