
ሀዋሳ ሰኔ 12/2017 (ኢዜአ) በሲዳማ ክልል የእንስሳት መኖን ጨምሮ በዘርፉ የሚያጋጥሙ የግብዓት እጥረቶችን በዘላቂነት ለመቅረፍ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡
የቢሮ ኃላፊው አቶ ተክሌ ጆምባ ለኢዜአ እንደገለጹት በክልሉ መኖን ጨምሮ በዘርፉ የግብዓት እጥረት እንዳያጋጥም በእቅድ የታገዙ ተግባራት እየተከናወኑ ነው፡፡
በክልሉ ያጋጠመውን የመኖ ዋጋ መናርና አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ አርሶ አደሩ በጓሮ መኖ እንዲያለማ የማድረግና የመኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎችን የማስፋፋት ስራ በትኩረት እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡
በተያዘው ዓመት በቀን 1 ሺህ 600 ኩንታል የሚያመርት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ወደ ስራ መግባቱን የገለጹት ኃላፊው በቀጣዩ በጀት ዓመትም አምስት ፋብሪካዎች ወደ ስራ እንደሚገቡ ገልጸዋል ፡፡
በክልሉ ያለውን የመኖ ተደራሽነት ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍም የህብረት ስራ ማህበራት በየወረዳው በማቋቋም ለአርሶአደሩ እንዲያሰራጩ ይደረጋል ብለዋል፡፡
በሌላ በኩልም ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባባር ከሃንጋሪ የመጡ 20 ሺህ ወላጅ ዶሮዎች ከሶስት ወር በኋላ ዝርያቸው የተሻሻሉ የአንድ ቀን ጫጩቶችን መፈልፈል እንደሚጀምሩ ተናግረዋል፡፡
በዚህም በክልሉ ያለውን የአንድ ቀን ጫጩት አቅርቦት ችግር በመቅረፍ እንደ ሃገር በዘርፉ ሞዴል ለመሆን በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
የእንስሳት በሽታን ለመቆጣጠርና ለመከላከል የሚያስችል የእንስሳት ጤና ላቦራቶሪ በተያዘው ዓመት መቋቋሙን ኃላፊው ገልፀው በተለያዩ አካባቢዎች የእንስሳት ጤና መከታተያ የህክምና ማእከላትም አገልግሎት መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡
ቢሮው በቀጣይ ዓመት ከሚተገብራቸው በርካታ እቅዶች መካከል በእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ዘርፍ የሚያጋጥሙ የግብዓት እጥረቶችን መቅረፍ ቀዳሚው መሆኑን አቶ ተክሌ ተናግረዋል፡፡
የግብዓት እጥረቶችን በዘላቂነት ለመቅረፍም በቴክኖሎጂ የታገዘ ስራ ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ጠቅሰው ለዚህም ከቴክኒክና ሙያ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
በይርጋለም ከተማ አስተዳደር የሚገኘው ጋኔ የዶሮ እርባታ ኃላፊነቱ የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ መላኩ እንየው ማህበሩ በ5 ሺህ የአንድ ቀን ጫጩት ወደ ስራ መግባቱን አስታውሰዋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም በቀን እስከ 4 ሺህ 500 እንቁላል ለገበያ በማቅረብ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱን እያረጋገጠ መሆኑን ጠቅሰው ለ30 ሰዎች የስራ እድል መፍጠሩን ተናግረዋል፡፡
10 ሺህ የአንድ ቀን ዶሮ ጫጩቶችን ለመቀበል የቦታ ዝግጅት ማድረጋቸውን ጠቅሰው መኖን ጨምሮ የግብዓት እጥረቶች ቢቀረፉ በተሻለ አምርተው የበለጠ ተጠቃሚ መሆን እንደሚሆኑም ተናግረዋል፡፡
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026