ሀዋሳ፤ ሰኔ 17/2017(ኢዜአ)፦ በዘንድሮው የመኸር ወቅት እርሻ ስራ ውጤታማ ለመሆን ተግተው እየሰሩ መሆናቸውን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስልጤና ጉራጌ ዞን አርሶ አደሮች ተናገሩ።
በክልሉ ለመኸር እርሻ የሚሆን የአፈር ማዳበሪያና ምርጥ ዘር በበቂ ሁኔታ እየቀረበ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ ገልጿል።
በ2017/18 የመኸር ወቅት ከ560 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች በመሸፈን ከ54 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱንም አስታውቋል፡፡
ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የስልጤና የጉራጌ ዞን አርሶ አደሮችና የግብርና ባለሙያዎች በ2017/18 የመኸር ወቅት እርሻ ተገቢውን ምርት ለማግኘት መሬትን ደጋግሞ በማረስና በማለስለስ ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን ገልፀዋል።
በስልጤ ዞን ምዕራብ አዘርኔት በርበሬ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር አብራር ሙስጤና አርሶ አደር አኑዋር ሸምሱ እንዳሉት የበልግ ወቅት ጨርሰው የመኸር እርሻን ውጤታማ ለማድረግ መሬት የማለስለስና ሌሎች ቅድመ ዝግጅቶች እያደረጉ ናቸው፡፡
ሌላኛው አስተያየት ሰጪ በጉራጌ ዞን በእኖር ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር ወልዴ ተክሉ በበኩላቸው በኩታ ገጠም ማሳ ለአምስት ሆነው 10 ሄክታር መሬት በቅንጅት እያለሙ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በበልግ በቆሎና ጤፍ በማምረት ውጤታማ መሆናቸውን አንስተው ለመኸርም የተሻለ ውጤት ለማግኘት ማሳቸውን ዝግጁ እያደረጉ መሆኑንና ዘንድሮ የአፈር ማዳበሪያና ምርጥ ዘር በበቂ ሁኔታ እንደቀረበላቸው ገልጸዋል፡፡
በዞኑ የጉመር ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር ሀሰን ነስሩ በበኩላቸው ያላቸውን ግማሽ ሄክታር ማሳ በገብስ ለመሸፈን በትራክተር ታግዘው እያረሱ መሆኑን ተናግረዋል።
የወረዳው የግብርና ባለሙያ ነስሮ ሰዒድ የመኸር እርሻን ውጤታማ ማድረግ በሚያስችል መልኩ የግብርና ግብዓት አቅርቦት ማቀላጠፍ ለአርሶ አደሩ ስልጠና ከመስጠት ጀምሮ የማሳ ዝግጅትና ሌሎች ድጋፎች እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረት ስራ ልማት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ተመስገን ጎደቦ፣ ለበጀት ዓመቱ በዕቅድ ከተያዘው 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ ከ790ሺህ ኩንታል በላይ የሚሆነው ለአርሶ አደሩ ተሰራጭቷል ብለዋል፡፡
የአርሶ አደሩን ውጤታማነት ለማረጋገጥ በዘንድሮ ዓመት የግብርና ግብዓት ከሌሎች ጊዜያት በተሻለና በተቀናጀ መልኩ መቅረቡንም አስረድተዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025