
ሮቤ ፤ ሰኔ 18/2017(ኢዜአ)፡-በባሌ ዞን በዘንድሮ የበልግ እርሻ ከ257 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ የሰብል ዘሮች መልማቱን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
በባሌ ዞን የበልግ እርሻ ወቅት ከመጋቢት አጋማሽ እስከ ነሐሴ ያለውን ጊዜ የሚያጠቃልል መሆኑ ይታወቃል።
በዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት የሰብል ልማት ባለሙያ አቶ ደረጀ ግርማ እንዳሉት፣ በዞኑ በዘንድሮ የበልግ እርሻ ከ257 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ የሰብል ዘሮች ለምቷል።
በዞኑ ከለማው የእርሻ መሬት መካከል ከ70 በመቶ የሚበልጠው የተሻሻሉ የግብርና አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ በኩታ ገጠም የለማ መሆኑንም አመልክተዋል።

አርሶ አደሩ የምግብ ዋስትናውን ለማረጋገጥ ከሚያደርገው ጥረት በተጓዳኝ የሀገር ውስጥና የውጪ ገበያ አማራጮችን ጭምር ታሳቢ በማድረግ እንዲያመርት ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም በበልጉ ወቅት እየለማ ከሚገኘው አጠቃላይ መሬት መካከል ከ40 ሺህ ሄክታር የሚበልጠው ገበያ ተኮር በሆኑ ሰሊጥ፣ ማሾ፣ ቦሎቄና የለውዝ ምርቶች መልማቱን በማሳያነት አንስተዋል።
የዘንድሮ የዝናብ ስርጭት በተለይም በቆላማ አካባቢዎች ጥሩ ስርጭት ስለነበረው ሰብሉ በጥሩ ቁመና ላይ መሆኑንና በአርሶ አደሩ እንክብካቤ እየተደረገለት እንደሚገኝ አስረድተዋል።
ከዋና ዋና ሰብል ልማቱም 8 ነጥብ 1 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማምረት ግብ መቀመጡንም ባለሙያው ተናግረዋል።
በዞኑ የሲናና ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርናና መሬት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሙአውያ ፉዓድ በበኩላቸው እንዳሉት፣ በወረዳው በዘንድሮ የበልግ ወቅት 50ሺህ ሄክታር መሬት በስንዴ፣ ገብስና ሌሎች ሰብሎች ለምቷል።

በተለይም በዘንድሮው የበልግ አዝመራ የአርሶ አደሩን የግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ይበልጥ ለማሻሻል በተቀመጠው ግብ መሰረት ከአጠቃላይ ልማቱ 60 በመቶ የሚበልጠው መሬት የተሻሻሉ አሰራሮችን በመጠቀም በኩታ ገጠም መልማቱን ተናግረዋል።
በልማቱ እየተሳተፉ ከሚገኙ የሲናና ወረዳ አርሶ አደሮች መካከል አቶ ሐሰን አህመድ በሰጡት አስተያየት፣ በባለፈው የመኽር እርሻ ከአንድ ሄክታር መሬት ከ60 ኩንታል በላይ የስንዴ ምርት መሰብሰባቸውን ተናግረዋል።
በዘንድሮ የበልግ ወቅት የተሻሻሉ የግብርና አሰራሮችን በመጠቀም የተሻለ ምርት ለመሰብሰብ የሚያስችል የሰብል እንክብካቤ እያደረጉ መሆናቸውንም አክለዋል።
አዲስ አበባ፤ሰኔ 2 /2018 (ኢዜአ)፦የዕቃ ማከማቻ ደረሰኝ ሥርዓት ደንብ የግብርና ኢኮኖሚ ሽግግርን በማሳለጥና የገጠር ልማትን በማጎልበት አርሶ አደሮችን ተጠ...
Jun 10, 2026
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 1/2018 (ኢዜአ)፦ በመዲናዋ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን በማላቅ የተገልጋዮችን እርካታ የሚያሳድጉ ሰው ተኮር ተግባራት ተጠናክረው እንደ...
Jun 9, 2026
ሀዋሳ ፤ ግንቦት 28/2018 (ኢዜአ) ፦በይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ማቀነባበሪያ ፓርክ ከአምራች ኢንዲስትሪዎች ጋር በተፈጠረላቸው የገበያ ትስስር ...
Jun 6, 2026
ነገሌ ቦረና፤ ግንቦት 19/2018(ኢዜአ)፦ የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት መጀመር የአካባቢውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የበለጠ የሚያ...
May 28, 2026