አዲስ አበባ፤ሰኔ 17/2017 (ኢዜአ)፦ የ2025 የአፍሪካ የቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ዘርፍ የአሰራርና ቁጥጥር ስርዓት ደህንነት ጉባዔና ስልጠና ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ገለጸ።
በኮሚሽኑ አዘጋጅነት "ጠንካራ የቁጠባና ብድር ኀብረት ሥራ ዘርፍ የአሰራርና የቁጥጥር ሥርዓት ለተረጋጋ የፋይናንስ ተደራሽነት" በሚል መሪ ሀሳብ ለሶስት ቀናት ይካሄዳል ተብሏል።
በጉባኤና በስልጠናው ለሚሳተፉ እንግዶች ዛሬ ማምሻውን በብሔራዊ ቤተ መንግሥት የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ስነ-ስርዓት ተካሂዷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ(ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሺፈራው ሽጉጤ (ዶ/ር)፣የልማት አጋሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ከአፍሪካ 24 አገራት፣ሰሜን አሜሪካና አውሮፓ የሚወከሉ ተሳታፊዎች በሚታደሙበት በዚህ የስልጠና መድረክና ጉባዔ በቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት አሰራርና ቁጥጥር ቁልፍ ጉዳዮችና ተግዳሮቶች ላይ ውይይት ይደረጋል።
በማህበራቱ አሰራር ወጥነት፣ግልጸኝነትና አስተማማኝነት ያለው ስርዓት መፍጠር ላይ ያጠነጠነ መሆኑም ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሺፈራው ሽጉጤ (ዶ/ር)፥ ጉባኤውን የአፍሪካ የአንድነትና ትብብር ምልክት በሆነችው አዲስ አበባ ማስተናገድ በመቻላችን ለኢትዮጵያና ለኮሚሽናችን ትልቅ ክብር ነው ብለዋል፡፡
ይህ አህጉራዊ ጉባዔና ስልጠና ለአፍሪካ የኅብረት ሥራ ንቅናቄ በወሳኝ ጊዜ የተዘጋጀ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ዘርፉን ከተለምዷዊ መዋቅር ወደ ዘመናዊ አመራርና አሰራር የሚከተል፣ ተወዳዳሪ ተቋም ለማሸጋገር በሚደረገው ጥረት አወንታዊ ሚና እንደሚጫወትም አክለዋል።
ኢትዮጵያ የኅብረት ሥራ ማህበራት ሪፎርም በማድረግ ላይ መሆኗንም አንስተዋል።
በመድረኩ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ኅብረት ሥራ ዘርፍ ህጋዊ ማዕቀፍ ለማሻሻል እያከናወነች ያለውን የሪፎርም ስራዎች ይቀርባሉ ብለዋል።
መድረኩ አዳዲስ ሀሳቦች ለመለዋወጥ፣ ውጤታማ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን ለመጠቀምና ከአፍሪካ ሀገራት ጋር አጋርነት ለመፍጠር መልካም አጋጣሚ ነው ብለዋል፡፡
የቁጠባና ብድር ኀብረት ሥራ የአሰራር ደንብ ማዕቀፍን ለማጠናከር፣ አዳዲስ የፋይናንስ አሰራር ስርዓት ለመፍጠርና የቁጥጥርና ክትትል ስርዓትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ አጋዥ እንደሚሆንም ጠቁመዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025