የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ኢትዮጵያ የጨረር ህክምና ተደራሽነትን ማስፋት የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነች ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

Jul 1, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 23/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የካንሰር ምርመራን ጨምሮ የጨረር ህክምና ተደራሽነትን ማስፋት የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነች መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

የጤና ሚኒስቴር ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ጋር በመተባበር "የተስፋ ጨረሮች በሚል መሪ ሃሳብ ያዘጋጁትና አቶሚክ ኢነርጂ በጤናው ዘርፍ ባለው ጠቀሜታ ዙሪያ የሚመክር ዓለም አቀፍ ጉባኤ በአፍሪካ ህብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ መካሄድ ጀምሯል።

በመድረኩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ጀነራል ራፋኤል ግሮሲ፣ ሚኒስትሮች፣ አምባሳደሮች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮችና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ታድመዋል።


ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በዚሁ ወቅት፥ የዓለም የጤና አውድ እየተቀየረ መሆኑን ጠቅሰው ኢትዮጵያም ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን ታሳቢ ያደረገ የጤና ስርዓት እየገነባች ነው ብለዋል።

ባለፉት ዓመታት በጤና ኤክስቴንሽን አማካይነት በተሰራው ስራ የበርካቶችን ጤና አጠባበቅ ማሻሻል መቻሉን ገልጸዋል።

በርካታ የጤና ባለሙያዎችም ሰልጥነው አገልግሎት እየሰጡ ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በሁሉም አካባቢ የጤና አገልግሎትን በጥራት ተደራሽ የማድረግ ጉዞ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።

ኢትዮጵያ የካንሰር ምርምራና የጨረር ህክምና ተደራሽነትን ማስፋት የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነች እንደምትገኝ በማንሳት፥ ለዚህም ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም መጀመሯን ጠቁመዋል።

የጨረር ህክምና በጥንቃቄ እና በኃላፊነት ጥቅም ላይ መዋሉን ለማረጋገጥ ጠንካራ የቁጥጥር ስርዓት መዘርጋቱን አመላክተዋል።

የኑክሌር ኢነርጂን ለጤና አገልግሎት በማዋል የጨረር ህክምናን ማስፋት የካንሰር በሽታን በፍጥነት በምርመራ በመለየት የሰዎችን ህይወት ለመታደግ ትልቅ ሚና እንዳለውም ነው የገለጹት።


ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አያይዘውም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የህብረተሰብን ጤና በማሻሻል ንቁና ጤናማ አኗኗርን እያጎለበተ መሆኑን አንስተዋል።

የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ የኑክለር ኢነርጂን ለሰላማዊ አገልግሎት በተለይም ለጤናው ዘርፍ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያደርጋቸው ድጋፎች የሚበረታቱ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

የልማት አጋሮች እና መንግስታት ከፈንድ ባሻገር የዓለም ጤና ውጤት ፈጣሪዎች በመሆን የትብብር አድማሳቸውን ከፍ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ ነው</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...

Feb 28, 2025

<p>በዞኑ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ ነው</p>

ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...

Feb 24, 2025

<p>የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተደረገ ነው - ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል</p>

አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...

Feb 24, 2025

<p>ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች ነው -የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...

Feb 12, 2025