አዲስ አበባ፤ ሰኔ 21/2017(ኢዜአ)፦ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሀገራቸውን ብሔራዊ ጥቅም በማስጠበቅና በልማት እያደረጉ ያለውን አስተዋጽኦ የበለጠ እንዲያጠናክሩ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲማ ኖጎ(ዶ/ር) ጥሪ አቀረቡ።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና ከውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሃላፊዎች የዳያስፖራውን ተሳትፎ በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ምክክር አካሂዷል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዲማ ኖጎ(ዶ/ር) ዳያስፖራው የሀገሩን ብሔራዊ ጥቅም በማስከበርና በልማት በመሳተፍ ሚናው የጎላ እንደሆነ አንስተዋል።
በተለያዩ የውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ብሔራዊ ጥቅምን በሚያስከብሩ ጉዳዮች ላይ በመሳተፍ ለሀገራቸው በተለያየ ዘርፍ የሚያደርጉትን አስተዋፅኦ እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል።
ዳያስፖራው በሬሚታንስ፣ በኢንቨስትመንትና በበጎ አድራጎት እያደረገ ያለውን አስተዋጽኦ የበለጠ ለማሳደግ በሚወጡ ህጎች የዳያስፖራውን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ትኩረት እንዲሰጡ ይደረጋል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍጹም አረጋ እንደተናገሩት በተለያዩ የውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ እየጨመረ ነው።
በኢንቨስትመንት፣ በሬሚታንስ፣ በበጎ አድራጎትና በልማት ስራዎች ላይ የሃሳብና የገንዘብ፣ እንዲሁም በቱሪዝምና በሌሎች ዘርፎች ተሳትፏቸው እየጨመረ መምጣቱን ነው ያስረዱት።
በሀገር የኢኮኖሚ እድገት ላይ ያላቸውን ተሳትፎ የበለጠ ለማሳደግ የአሰራር ማሻሻያዎች እየተደረጉ መሆኑንም አምባሳደር ፍጹም ተናግረዋል።
አሰራርን ከማዘመን አንጻር የኦንላይን ቪዛ አገልግሎት፣ ውክልና እና ሰነድ ማረጋገጥን በሚመለከት የሚወስደውን ረጅም ጊዜ በማሳጠር በ24 ሰዓት ማረጋገጥ የሚቻልበት ስርዓት ተዘርግቷል ብለዋል።
የምክር ቤት አባላት ወደ ምርጫ ክልላቸው በሚሄዱበት ወቅት የዳያስፖራ ጉዳይ የሚስተናገድበትንና በስራ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ሂደት ክትትል እንዲያጠናክሩም ጠይቀዋል።
የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ እንደተናገሩት የውጭ ግንኙነት ስራ በዲፕሎማቶች ብቻ የሚሰራ ባለመሆኑ የዳያስፖራውን ሚና ለማሳደግ እየተሰራ ይገኛል።
የቋሚ ኮሚቴ ሃላፊዎችበበኩላቸው፥ ዳያስፖራው በኢንቨስትመንትና በሌሎች የልማት ስራዎች ላይ በሚያደርገው ተሳትፎ የሚያጋጥሙ የአሰራር ማነቆዎችን ለመፍታት ክትትልና ቁጥጥራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ዳያስፖራው በሀገራዊ ዕድገት ውስጥ ተጠቃሚ እንዲሆን የተሰጠው ትኩረትና የተደረጉ የህግ ማሻሻያዎች ለውጥ እያመጡ ነው ብለዋል።
በመድረኩ በዳያስፖራና ኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ እንዲሁም ፍልሰት አስተዳደር ላይ ትኩረት ያደረጉ ሀሳቦች ላይ ውይይት ተደርጓል።
ዓላማውም የምክር ቤት አባላት በክረምት የእረፍት ጊዜ ወደ ምርጫ ክልላቸው በሚሄዱበት ወቅት በዳያስፖራ ዙሪያ መነሳት ያለባቸው ጉዳዮችና ከሀገር ውጭ ለስራ በሚሄዱበት ወቅትም ትኩረት ማድረግ ያለባቸውና የሚያስፈልጉ ድጋፎች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ነው ተብሏል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025