አዳማ ፤ ሰኔ 22/2017(ኢዜአ) የጤፍ ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ እሴት በመጨመር ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ገለፀ።
በጤፍ ሰብል ልማትና እሴት ጨምሮ ማምረት ላይ የተሰማሩ ባለድርሻ አካላት የጋራ የምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ ተካሂዷል።
በግብርና ሚኒስቴር የሰብል ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ኢሳያስ ለማ ለኢዜአ እንደገለጹት በኢትዮጵያ ከሁለት ሚሊዮን በላይ አርሶ አደሮች በጤፍ ልማት ላይ ተሰማርተዋል።
እነዚህን አርሶ አደሮች ተጠቃሚ ለማድረግ የጤፍን ምርትና ምርታማነት ከማሳደግ ባለፈ እሴት ጨምሮ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ጤፍን የኢትዮጵያ ቀዳሚ ምርት ለማድረግ ግብ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ያመለከቱት አቶ ኢሳያስ፤ "የጤፍ ምርታማነት አናሳ መሆን፣ የምርጥ ዘርና የግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ክፍተት የዘርፉ ማነቆዎች ናቸው ብለዋል።
በዓለም ምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ረዳት ተወካይ ወርክቾ ጃተኖ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በጤፍ ልማት ላይ የጥናትና ምርምር ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቁመዋል።
በጤፍ ምርትና ምርታማነት ላይ የሚደረግ ምርምር በሚፈለገው ደረጃ ያለመሆንና ጤፍን በሜካናይዜሽን ግብርና ለማልማት የማሽነሪዎች እጥረት መኖር በጥናት መለየቱን ገልጸዋል።
"የአንድ ሀገር ተቀዳሚ ምርት" የሚል ፕሮጀክት በመቅረጽ በጤፍ ምርት ላይ የምርምርና የአቅም ግንባታ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የጤፍ ሰብል ከፍተኛ ተመራማሪ ሀብቴ ጁፋር (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ የጤፍ ምርትና ምርታማነት ማነቆዎችን ለመፍታት ከግብርና ሚኒስቴርና ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ጋር በትብብር እየሰራን ነው ብለዋል።
በዚህም በጤፍ ዝርያ ማሻሻል፣ በተመራማሪዎች አቅም ግንባታ እንዲሁም በጤፍ ምርትና ምርታማነት የባለድርሻ አካላት ፕላት ፎርምን ጭምር በማዘጋጀት እየሰሩ መሆናቸውን አስረድተዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025