አዲስ አበባ፤ ሰኔ 23/2017(ኢዜአ)፦ ከ18 ማዞሪያ - አሸዋ ሜዳ - ኬላ መንገድ ባለው መስመር እየተከናወነ የሚገኘው ከ14 ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ፕሮጀክት እየተፋጠነ መሆኑን በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አስታወቀ፡፡
የመንገድ ፕሮጀክቱ የአዲስ አበባ - አምቦ - ነቀምት መስመር አካል ሲሆን፥ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ዕድገት ታሳቢ በማድረግ ደረጃውን በጠበቀ መንገድ እየተሰራ መሆኑን አስተዳደሩ ገልጿል።
ኢዜአ የመንገድ ፕሮጀክቱን የግንባታ ሥራ ቅኝት በማድረግ የፕሮጀክቱን ኃላፊዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን አነጋግሯል።
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የፕሮጀክት አስተባባሪ ኢንጂነር ዮሀንስ ሲሳይ እንደገለጹት፥ ፕሮጀክቱ 14 ነጥብ 72 ኪሎሜትር የሚሸፍን ሲሆን፥ በተጀመረ በሶስት ወራት ውስጥ የግንባታ ሂደቱ 20 በመቶ ደርሷል።
የመንገድ ግንባታው በጥቂት ጊዜ ውስጥ ትላልቅ የሚባሉ ስራዎች የተከናወኑበት መሆኑን አንስተው በዚህ ዓመት መጨረሻ ድረስ የአስፋልት ማንጠፍ ስራ እንደሚከናወን አስታውቀዋል፡።
መንገዱ የከተሞችን ዕድገት፣ የማህበረሰቡን ዘመናዊ አኗኗር ታሳቢ ባደረገ መልኩ እየተገነባ የሚገኝ ስማርት የመንገድ ፕሮጀክት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የመንገድ ፕሮጀክቱ አጠቃላይ ስፋቱ 66 ሜትር ሲሆን ከዚህ ውስጥ የአስፋልት መንገዱ ስፋት 50 ሜትር መሆኑን ጠቅሰው፥ የእግረኛ፣ የብስክሌት፣ የመሮጫ መም እና አረንጓዴ ስፍራዎችን ማካተቱንም ገልጸዋል።
የመንገድ ፕሮጀክቱ ከፍተኛ የተሽከርካሪ ፍሰት ባለበት፣ ከፍተኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በሚደረግበት አካባቢ እየተገነባ በመሆኑ በአፋጣኝ ለማጠናቀቅ ቀን ከሌሊት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የትራፊክ ፍሰቱን ከማሳለጥ በተጨማሪ በርካታ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ይዞ እንደሚመጣም ገልጸዋል፡፡
የፕሮጀክቱ ተቆጣጣሪ ኢንጂነር ተካልኝ አስራት በበኩላቸው መንገዱ ጥራቱን የጠበቀ እንዲሆን ከፍተኛ ሥራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።
የምርት እንቅስቃሴን በፍጥነት ወደ ገበያ ተደራሽ ለማድረግ በሚያስችል መልኩ በርካታ ተሽከርካሪዎችን በአንድ ጊዜ ማሳለፍ የሚያስችልና ለሀገር አቀራጭ መንገዶች መጋቢ መንገድ መሆኑን ገልጸዋል።
ከዲዛይን አንጻር ከፍተኛ የሚባለውን ደረጃ ያሟላ መሆኑን ገልጸው፥ በሦስት ደረጃ የአስፋልት ንጣፍ እንደሚሰራለት ተናግረዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በሁለት ሀገር በቀል ተቋራጮች እየተገነባ መሆኑን አንስተው ይህም የሀገራችን የግንባታ ተቋራጮች ትላልቅ ፕሮጀክቶችን በአግባቡ የመፈጸም ትልቅ አቅም እንዳላቸው ማሳያ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
ከዚህ ቀደም ከ18 ማዞሪያ እስከ ኬላ ያለው መንገድ የትራፊክ መጨናነቅ ያለበት በመሆኑ ካሰቡት ለመድረስ ረጅም ጊዜን የሚጠይቅ እንደነበር ያነሱት በአካባቢው ሲያሽከረክሩ ያገኘናቸው ሙሉጌታ ጉልማ እና ጌታቸው ቢያድግ ናቸው።
አዲሱ የመንገድ ግንባታ ሲጠናቀቅ የትራፊክ እንቅስቃሴውን በማሳለጥ አሽከርካሪዎች በቀላሉና በአጭር ጊዜ የፈለጉበት ቦታ እንዲደርሱ በማገዝ እፎይታን ይሰጣል ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025