አዲስ አበባ፤ ሰኔ 25/2017(ኢዜአ)፦ በአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ጥራት ቁጥጥርና አደጋ አስተዳደር የሰለጠኑ 40 የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ባለሙያዎች ዓለም አቀፍ የምስክር ወረቀት ማግኘታቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ።
አገልግሎቱ ለኢዜአ በላከው መረጃ እንዳመለከተው፤ በኢትዮጵያ አጠቃላይ የአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ስራዎችን በበላይነት ለመምራት በአዋጅ ኃላፊነት የተሰጠው ተቋሙ ከዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) ጋር በመተባበር በአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ ጥራት ቁጥጥርና በአቪዬሽን አደጋ አስተዳደር ዙሪያ ስልጠና የወሰዱ 40 ባለሙያዎች ዓለም አቀፍ የምስክር ወረቀት እንዲያገኙ ማድረጉን ገልጿል።
የዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ከ12 ዓመታት በኋላ በኢትዮጵያ የአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ አሰራሮች ላይ ባደረገው ኦዲት ሀገራችን ምንም ዓይነት የሴኪዩሪቲ ስጋት እንደሌለባት ማረጋገጡን አስታውሷል።
ይህን ተከትሎም ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የሲቪል አቪዬሽን ደኅንነት ዋና መምሪያ ጋር በተፈጠረው መልካም ግንኙነትና ትብብር ስልጠናው ከዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት በመጡ ባለሙያዎች ከሰኔ 9 እስከ ሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሰጥቷል።
ዓለም አቀፍ የምስክር ወረቀቱ አየር መንገዱ ተደራሽ በሚሆንባቸው ሀገራት ሁሉ የአቪዬሽን ሴኪዩሪቲ የጥራት ቁጥጥር ተግባራትን ለማካሄድ የሚያስችል መሆኑን የገለጹት ከዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት የመጡት አሰልጣኞች፤ ባለሙያቹ ስልጠናውን በስኬት ማጠናቀቃቸውን ጠቁመዋል።
ስልጣኞች ያገኙት ዕውቀት ተቋሙ ሀገራዊ ተልዕኮውን በላቀ ብቃት ለመፈፀም የሚያስችለው ከመሆኑም ባለፈ፤ ኢትዮጵያን ለአቪዬሽን ደህንነት ዘርፍ እየሰጠች ያለችው ልዩ ትኩረት ጉልህ ማሳያ ተደርጎም ሊወሰድ እንደሚችል የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አመልክቷል።
የአቪዬሽን ደህንነት ጠንካራ የጥራት ቁጥጥር ትግበራ እና የአደጋ ምላሽ አሰጣጥ ዝግጁነት የእያንዳንዱ የዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት አባል ሀገራት ኃላፊነት መሆኑን ያስታወቀው አገልግሎቱ ፤ ይህም የአቪዬሽን ኢንዱስትሪውን ደኅንነት በዓለም አቀፍ ስታንዳርድ መሰረት ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ገልጿል፡፡
በስልጠናው የተገኘውን ዕውቀት፣ ክህሎት እና የአስተሳሰብ ለውጥ በቀጣይ በአቪዬሽን ደህንነት ዘርፍ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለመሆን ለተያዘው ራዕይ እና አጠቃላይ ተቋማዊ ስትራቴጂ ግብዓት አድርጎ በማዋል የኢትዮጵያ አየር መንገድን ተመራጭነት ይበልጥ በማሳደግ ሀገራዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረው አገልግሎቱ ለኢዜአ በላከው መረጃ አስታውቋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025